ኮርት ማናጀር ጽ/ቤት

አቶ የምስራች ከተማ

ኮርት ማናጀር ጽ/ቤት

በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • የአስተዳደር ዘርፉን /ፋይናንስን፣ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ፣የሰው ሀብት /እቅድ ዝግጅ ክትትል እና ግምገማ ፣ኢኮቴ እና ጠቅላላ አገልግሎትን በበላይነት ይመራል
  • ዳይሬክቶሬቶች ዕቅድ ማቀዳቸውን ፣ስራዎችን በዕቅድ መመራታቸውን እና ሪፖርት ሲያቀርቡ ተግባራቸውን ይከታተላል፡፡

ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት

ወ/ሮ ዙፋን ወ/ገብርኤል

ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት

  • በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • በምድብ ችሎቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ከምልልስ የፀዱ እንዲሆን በማድረግ የሚሰጡትን አገልግሎቶች ለማግኘት በጉዳዮች ምን ቅድመ-ሁኔታዎችን ማሟላት እንዳለባቸው እንዲያውቁ የሚያስችሉ ማስታወቂያዎችን መለጠፋቸውን፣ የአንድ መስኮት አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የተዘረጋላቸው ምድብ ችሎቶች አገልግሎቶች አንድ መስኮት በኩል እየተሰጠ መሆኑን፣ ትዕዛዝ፣ ብይን፣ ውሳኔ እና የይግባኝ ግልባጭ በተቻለ መጠን በመረጃ ዴስክ በኩል እየተሰጡ መሆኑን እና ፍርድ ቤቱ ባወጣው ጊዜ ሰሌዳው መሠረት እየተሰጠ መሆኑን በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት ይከታተላል፡፡ 

የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ወ/ሮ የክቴ ዋለ

የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

  • በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • የዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ማቀድ፣ ማደራጀት፣ መምራት፣ መከታተል፣ መደገፍ መወሰን መቆጣጠር፣ የስራ አፈጻጸም መገምገም፣ ክፍተቶችን መለየት፣ ማብቃት፡፡
  1. በተቋሙ አደረጃጀት መሠረት ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውውር፣ የዲስፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡

ግዢና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት

አቶ ሰለሞን ፈጠነ

ግዢና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት

  • በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • ዳይሬክቶሬቱን ተግባራት ያቅዳል ያደራጃል ፣ይመራል፣ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል
  • በተቋሙ ጤናማ የግዢና ንብረት አስተዳደር ስርዓት እንዲዘረጋ ያደርጋል፡፡
  • የግዢ ንብረት አስተዳደር ትግበራ የሚመለከቱን ደንብና እና መመሪዎች በስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፡፡

ፋይናንስ ዳሬክቶሬት

ወ/ሮ ታደለች ጥላሁን

ፋይናንስ ዳሬክቶሬት

በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  1. የዳኝነት ተመላሽ የቅጣት ተመላሽ እና የትርጉም ተመላሽ
  2. 2. የመስተንግዶ ውሎ አበልና ትራንስፖርት ስልጠና
  3. 3. ለነዳጅ ቅባት ለመኪና ሰርቪስ ለኮሚፐተር ፕሪነተር ፎቶ ኮፒ ጥገና
  4. 4. የቤት ክራይ የተለያዩ በውል የሚካፈሉ ለግንባታ እና ለህንፃ እድሳት
  5. 5. አላቂና ቋሚ የፅህፈት መሳሪያና ለፅዳት አገልግሎት ለቋሚ እቃዋች

እቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳሬክቶሬት

አቶ ኸሊል ነጋሽ

እቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳሬክቶሬት

  • በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • የተቃሙን ዕቅድ ያቅዳል እስከ ፈጻሚ በማውረድ ያሳቅዳል ድጋፍ ያደርጋል፤ ያስተባብራል የ ስራ አፈጻጸም ይመዝናል ፡፡
  • የአሰራር ችግሮችን በመለየት እና በማጥናት ምቹ የአሰራር ሂደት እድኖር ያደርጋል ተፈጻሚነቱንያረጋግጣል ፡፡
  • ተቃማዊ ለውጥ ና መልካም አሰተዳደደር ስራዎች ተግባራዊ ያደርጋል አድሆን ይከታተላል ምርጥ ተሞክሮ ይለያል ፤ይቀምራል ያሰፋል ፡፡

የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳሬክቶሬት

አቶ መሃመድ ጦይብ

የስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ዳሬክቶሬት

በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  1. የዳይሬክቶሬቱን የስራ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ ይገመግማል፤ ያስተባብራል፤ ይመራል፤ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡
  2. በተቋሙ ውስጥ ለሙስና እና ለብልሹ አሰራር ክፍተት የሚፈጥር አሰራሮችን በጥናት ይለያል፤ የአሰራር ክፍተቶችን ሊያሟላ የሚችል ረቂቅ የስነምግባርና ብልሹ አሰራር ማንዋል እና የመተዳደሪያ ኮድ ኦፍ ኢቲክስ ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅም ያደርጋ፡፡

የኮሙዮኒኬሽን ዳሬክቶሬት

አቶ ዮናስ ሀበሻ

የኮሙዮኒኬሽን ዳሬክቶሬት

በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  1. ውጤታማ የሆነ የህዝብ ግኑኝነት እና ተግባቦት እስተራቴጅክ ዕቅድ እና በክፍሉ ሊ.ታቀዱ የሚ ችሉ ዕቅዶችን ያዘጋጃል ፡፡
  2. የተቃሙን የመረጃ ፍሰት የተስተካከለ በማድረግ የተለያዩ ሁነቶችን ላይ የመሳተፍ የማስተባበር ፤ በሁነቶች የተገኙ መረጃዎች በማጠናቀር ለህዝብ ግንኙነት ተግባቦት ስራ ማዋልና የተቋሙን መልካም ገጽታ መገንባት ፡፡

የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት

አቶ ሃጎስ ግርማይ

የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት

በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በስሩ ባሉት ሶስት ቡድኖች ማለትም የዳታቤዝ ቡድን፣ የኔትወርክ አስተዳደር ቡድን እና የኮምፒውተር ጥገና ቡድን አማካኝነት ከዚህ በታች የተጠቀሱት አገልግሎቶች/ስራዎች ይሰራል፡፡

ህግ ጥናት እና ድጋፍ ክፍል

በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  1. ከዳይሬክቶሬቱ እቅድ በመነሳት የክፍሉን የስራ እቅድ ያዘጋጃል፣ በዳይሬክቶሬቱ እቅድ ክለሳ ላይ ይሳተፍል፣ በእቅዱ መሰረት ስራዎችን ያከናውነናል፡፡
  2. ጥናት እና ምርምር ለማከናወን የሚያስችል ቢጋር (TOR) ያዘጋጃል፡፡

    ህግ ጥናት እና ድጋፍ ክፍል የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

  3. ከዳይሬክቶሬቱ እቅድ በመነሳት የክፍሉን የስራ እቅድ ያዘጋጃል፣ በዳይሬክቶሬቱ እቅድ ክለሳ ላይ ይሳተፍል፣ በእቅዱ መሰረት ስራዎችን ያከናውነናል፡፡
  4. ጥናት እና ምርምር ለማከናወን የሚያስችል ቢጋር (TOR) ያዘጋጃል፡፡

ኢንስፔክሽን ክፍል

  • በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  • በዳኘነት ዘርፍ ላይ የሚነሱ ቅሬታ እና አቤቱታዎችን መቀበል፣ ማጣራት እንዲሁም ለሚመለከታቸው የበላይ ኃላፊዎች ሪፖርት ማድረግ፤
  • ተከታታይ ከሚቀርቡ ቅሬታዎች በመነሳት በየሶስት ወሩ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ሪፖርት ማድረግ፤

የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል

አቶ ካሳሁን አሰፋ

የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል

በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  1. በመንግስት ተሽከርካሪዎች አጠቃቀም ደንብ እና መመሪያ መሰረት በማድረግ የተቋሙን ተሸከርካሪዎች በተገቢው ሁኔታ የትራንስፖርት ስምሪት አገልግሎት መስጠት
  2. የተቋሙን ተሸከርካሪዎች በወቅቱ ሰርቢስ እና ጥገና እንዲሁም ቅባት እና ነዳጅ እንዲያገኙ ማድረግ
  3. የአስተዳደር እና ሪከርድ መዝገብ ቤት የገቢ እና ወጭ ደብዳቤ አግባብነት ባለው መስራት እንዲሁም ተመላሽ ደብዳቤዎችን ፋይል ማድረግ

የሶሻል ወርክ ክፍል

ወ/ሮ ሙሉ ወንድሙ

የሶሻል ወርክ ክፍል

በጽ/ቤቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች

  1. የወንጀል ድርጊት ተጠቂ (ምስክር የሆኑ ህፃናትን ቃላቸውን ለፍ/ቤት በሚሰጡበት ወቅት የፍርሃት፣ መደናገር እና የመጨነቅ ስሜት እንዳይፈጠርባቸው ከህፃናቱ ጋር ጥሩ ግንኙነት በመፍጠር ስለ ፍ/ቤት አሰራር እና አከባቢ ማለማመድ፣ ስለመጡበትም ጉዳይ ምንነት (ለምስክርነት መሆኑን) ማሳወቅ እና የህፃናቱን የግል መረጃ መሰብሰብና ማደራጀት እና ለምስክርነት ማለማመድና እንዲዘጋጁ ማድረግ፡፡
  2. ከችሎት የሚነሱ ጥያቄዎች ህፃናቱ በሚረዱበት ቋንቋ (የሚቀርብላቸውን ጥያቄ እንደ ዕድገት ደረጃቸው ይዘቱን ባለቀቀ መልኩ እንዲረዱ አድርጎ ማቅረብ (ማስረዳት) ምስክርነቱን እንዲሰጡ ሙያው እገዛ ማድረግ፡፡