
ክብርት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ አሊቤ ሰኔ 12 ቀን 1978 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ተወልደው ያደጉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በምክትል ፕሬዝዳንትነት እያገለገሉ የሚገኙ ይገኛሉ፡፡
ወ/ሮ አሸነፈች በሕግ መስክ በቂ ልምድ ያላቸው ሲሆን ከአራት ዓመት በላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ የሕግ ማርቀቅ እና ምርምር ኦፊሰር እንዲሁም በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በዐቃቤ ህግነት አገልግለዋል፡፡ ከዚህ በመቀጠል በዳኝነት ተሾመው ከስድስት ዓመት በላይ በአዲስ አበባ ከተማ ፍ/ቤት እና በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አገልግለዋል፡፡
ወ/ሮ አሸነፈች በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ ከአዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የመጀመሪያ ዲግሪ በሊደርሺፕ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡