ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር አህመድ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር ሰኔ 2011 ዓ.ም በፓርላማው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሾሙ በኋላ በፍርድ ቤቱ በርካታ ስኬታማ ማሻሻያዎች እንዲመጡ አድርገዋል፡፡ ፍርድ ቤቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ባደረጉት ጥረት አዳዲስ የአሠራር መንገዶች ቀይሰዋል፤ ምቹ የሥራ ሁኔታ እንዲፈጠር ጥረት አድርገዋል፤ ከሠራተኞች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት በመሥራት ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ እዲመጣ በማሳየት እና፤ በፍርድ ቤቱ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣትም እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ክቡር አቶ ፉዓድ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊት በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የኢኮኖሚ ወንጀል ዳይሬክተር፣በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የአቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ረዳት ዳኛ ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት እና በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው አገልግለዋል
ክቡር አቶ ፉዓድ በስራ ዘመናቸው በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ውስጥ ያገለገሉ ሲሆን በብዙ መስሪያ ቤቶችም በነበራቸው የግዜ ቆይታ በስራቸውና እና በአመራር ብቃታቸው እንዲሁም በታታሪነታቸው የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በ2010 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት እንዲሁም በ2013 ከፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጣቸው ሽልማት ማሳያዎች ናቸው፡፡
ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በህግ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የተቀበሉ ሲሆን ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በፌዴራል ጥናቶች ወይም ፌዴራል እስተዲስ በከፍተኛ ማዕረግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመርቀዋል፡፡ ከመደበኛ ትምህርታቸው በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት የእውቅና ሰርቲፊኬት ያገኙ ሲሆን ለምሳሌ ከቤልጀም ብራስልስ የአለም ከስተም ድርጅት በግምሩክ ህግ ዙሪያ እንዲሁም ከፈረንሳይ ስትራትስበርግ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ኢንስቲትዉት በንፅፅዊ የአለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ የዕውቅና ሰርተፍኬት አግኝተዋል፡፡