በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

  1. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማን ነው?

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በህገ መንግስቱ የዳኝነት ስርዓትን እንዲሚፈፅሙ ወይም እንዲያከናውኑ ስልጣን ከተሰጣቸው ሦስቱ የዳኝነት ተቋማት (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት) አንዱ ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ የመጀመሪያ ጉዳዮች የሚታዩበት እንደመሆኑ መጠን ከፍተኛ የጉዳዮች ፍሰት የሚታይበት፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የሚስተናገድበት፣ ከፍተኛ ዳኞች፣ ሬጅስትራሮችና የአስተዳደር ሰራተኞች የሚገኙበት ተቋ ነው፡፡

2.  የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምን ያል ምድብ ችሎቶች አሉት?

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተደራሽነትን ለማስፋትና ችግሮችን በቅርበት ለመፍታት ያመቺ ዘንድ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች አስራ አንድ ምድብ ችሎቶችን በውስጡ የያዘ ፍርድ ቤት ነው፡፡

       3. የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚመለከለታቸው ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው?

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁሉንም የፍታብሔር፣ የወንጀልና የስራ ክርክር ጉዳዮችን ይመለከታል፡፡ ይሁን እንጂ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መቋቋሚያ አዋጅ 1234/2013 ስራ ላይ መዋሉን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ከዚህ በፊት ያይ ከነበረው የበለጠ እስከ አስር ሚሊዮን የሚገመት ጉዳይ እንዲያይ ያስችለዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም ቀድሞ በፍርድ ቤቱ ሲታዩ የነበሩ አንዳንድ ጉዳዮች ወደ ከተማ አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲዛወሩ ተደርጓል፡፡

      4. በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምን ያህል ችሎቶች አሉ?

ብዙዎች ጉዳዮች የሚታዩት በፌዴራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው፡፡ በአጠቃላይ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልዩ ልዩ፣ የቤተሰብ፣ የውርስ፣ የአፈፃፀም፣ የባንክና ኢንሹራንስ፣ የንግድ፣ የጉዲፈቻ፣ የመደበኛና መደበኛ ያለሆኑ ወንጀሎች፣ ጊዜ ቀጠሮ እና ስራ ክርክር ችሎቶች ይታያሉ፡፡