ተገልጋዮች ወደ ፍ/ቤት ሲመጡ ሊያሟሏቸው የሚገቡ ነገሮች

መዝገብ ለመክፈት

  • ለችሎት የሚቀርብ የፅሁፍ አቤቱታ በሀርድና በሶፍት ኮፒ፤
  • ከአቤቱታ ጋር ለተያያዙ ማስረጃዎች የቴምብር ቀረጥ የተከፈለባቸው መሆናቸውን የሚያሳይ ቴምብርና ማህተም ሊኖራቸው ይገባል፤
  • መዝገቡን የሚያስከፍተው ግለሰብ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/ፓስ ፖርት ወይም ውክልና ከሆነ አግባብነት ያለው የውክልና ውል ዋናው እና አንድ ኮፒ እንዲሁም የተወካይ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/ፓስፖረት ሊኖረው ይገባል፤

አቤቱታ ለችሎት ለማቅረብ

  • የችሎቱን የአቤቱታ ቀን ማወቅ፤
  • ለችሎት የሚቀርበውን አቤቱታ በፅሁፍ ማቅረብ፤
  • የባለ ጉዳይ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/ፓስፖርት ወይም በውክልና ከሆነ አግባብነት ያለው ውክልና ውል ዋናው እና አንድ ኮፒ እንዲሁም የተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት መቅረብ ይኖርበታል፤

ባለሙያ ለማስመደብ

  • ባለሙያ እንዲመደብ የታዘዘበት ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ ዋናውና አንድ ኮፒ፤
  • የባለ ጉዳይ የታደሰ የቀበሌ/ፓስፖርት መታወቂያ ወይም በውክልና ከሆነ አግባብነት ያለው ውክልና ውል ዋናውና አንድ ኮፒ እንዲሁም የተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስ ፖርት ሊኖር ይገባል፤

ውሳኔ ለውጭ ጉዳይ ተረጋግጦ ለመውሰድ

  • በጽሁፍ የቀረበ ማመልከቻ (መዝገብ ቁጥሩን፣ ውሳኔ የተሰጠበትን ቀን፣ ውሳኔውን የሰጠው ችሎትና ባለጉዳዮችን የሚገልፅ) መቅረብ ይኖርበታል፤
  • የባለጉዳዩ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/ፓስ ፖረት ወይም በውክልና ከሆነ አግባብነት ያለው ውክልና ውል ዋናውና አንድ ኮፒ እንዲሁም የተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስ ፖረት ሊኖር ይገባል፤

የትዕዛዝና የውሳኔ ግልባጭ ለመውሰድ

  • በፅሁፍ የቀረበ ማመልከቻ (መዝገብ ቁጥሩን፣ ውሳኔ የተሰጠበትን ቀን፣ ውሳኔውን የሰጠው ችሎትና ባለጉዳዮችን የሚገልፅ) ማቅረብ፤
  • የባለጉዳዩ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/ፓስፖርት ወይም በውክልና ከሆነ አግባብነት ያለው የውክልና ውል ዋናውና አንድ ኮፒ እንዲሁም የተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል፤

ዋስትና ለማስመለስ

  • ዋስትና የተያዘበት ደረሰኝ፤
  • ዋስትናው እንዲመለስ የተሰጠው ትዕዛዝ/ውሳኔ፤
  • ዋስትና ያስያዘው ግለሰብ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስ ፖርት አሊያም ውክልና ከሆነ የተወካይ አግባብነት ያለው ውክልና እና የተወካይ መታወቂያ/ፓስ ፖርት፤

የይግባኝ ግልባጭ ለመውሰድ

  • የይግባኝ አቤቱታው ላይ የይግባይኝ መዝገቡ እንዲቀርብ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር የተመራበት ይግባኝ አቤቱታ፤
  • የባለጉዳዩ የታደሰ የቀበሌ መታወቁያ/ፓስፖርት ውክልና ከሆነ ደግሞ አግባብነት ያለው የውክልና ውል ዋናውና አንድ ኮፒ እንዲሁም የተወካይ የታደሰ መታወቂያ/ፓስ ፖርት ሊኖር ይገባል፡፡

ጉዳይን በአስማሚ ለመጨረስ

  • ከችሎት የተሰጠ ትዕዛዝ፤
  • በተሰጠ ቀጠሮ ቀን እና ቦታ መገኘት፤
  • ጠበቃ ወይም ተወካይ ካልሆነ በስምምነት ለመጨረስ የሚያስችል ውክልና፤