ችሎት የሚጀመርበት ሰዓት

የተለየ ሁኔታ ወይም ምክንያት ከሌለ በቀር መደበኛ ችሎት ጠዋት ሶስት ሰዓት እና ከሰዓት ስምንት ሰዓት ይሰየማል፡፡

በችሎት ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት

በችሎት ውስጥ የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይከናወናሉ

1.   ክስ፣ መልስ፣ የፅሁፍ ማስረጃ፣ የተለያዩ አቤቱታዎችን እና አስተያየቶችን መቀበል

2.   ክስ፣ ሙግት/ክርክር፣ እና ምስክር መስማት

3.   ትዕዛዝ፣ ብይን፣ ፍርድ፣ ውሳኔ እና ቅጣት ማንበብ

የቃለ መሐላ አፈፃፀም

1.   ቃለ መሐላ እውነትን በማውጣት ረገድ ከፍተኛ ሚና ስላለው በህግ የመማል ግዴታ ያለበት ማንኛውም ሰው፣ ተከራካሪ ወገን፣ ምስክር ወይም አስተርጓሚ ሚሰጠው ቃል ወይም ምስክርነት ወይም ትርጉም እውነተኛ ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ ቃለ መሐላ በህጉ በተቀመጠው አግባብ ይፈፅማል፡፡

የችሎት ሂደትን ቆሞ ስለመከታተል

በችሎት ሂደት የክስ፣ የመልስ፣ የአቤቱታ እና የማስረጃ ልውውጥ ሲደረግ፤ ክስ፣ ክርክር፣ ወይም ምስክር ሲሰማ፤ ማንኛውም ሌላ ማመልከቻ፣ አቤቱታ፣ ቅሬታ ወይም የማጠቃለያ ንግግር ሲቀርብ፤ ትዕዛዝ፣ ብይን፣ ፍርድ፣ ዉሳኔ ወይም ቅጣት ሲነበብ ወይም ዳኛው ሌላ የችሎት ስራ ሲያከናውን ጉዳዩ የሚመለከተው ተከራካሪ ወገን ወይም ወኪል፣ ጠበቃ፣ ዐቃቤ ህግ፣ ነገረ ፈጅ ወይም ሌላ ሰው ለፍርድ ቤቱ ክብር ሲባል ጉዳዩን ቆሞ ይከታተላል፡፡ ሆኖም ችሎቱ እንደየሁኔታው በህመም፣ በአካል ጉዳት፣ በእድሜ መግፋት፣ በእርግዝና እና በሌሎች መሰል ምክንያቶች ቆሞ መከታተል የማይችል ሰው ካለ ወይም ክርክሩ ረዥም በሚሆንበት ጊዜ ከተከራካሪ ወገን ወይም በጋራ ክስ ካቀረቡት ወይም ከተከሰሱት ሰዎች መካከል ክርክር፣ ቅሬታ፣ አቤቱታ ወይም ምስክር የማያሰሙት እንዲቀመጡ ሊፈቅድ ይችላል፡፡

የአለባበስ ሥርዓት

     1. ማንኛውም ዳኛ ችሎት ሲሰየም የዳኛ ጋዋን/ካባ መልበስ አለበት፡፡

2. ማንኛውም በችሎት የሚገኝ እና ክርክር የሚያደርግ ዐቃቤ ህግ፣ ጠበቃ፣ እና ተከላካይ ጠበቃ ንፅህናውን የጠበቀ እና ያልተጨማደደ የዐቃቤ ህግ፣ የጠበቃ እና የተከላካይ ጠበቃ ጋዋን/ካባ መልበስ አለበት፡፡ ችሎት ውስጥ ጋወን መልበስ፣ መቀያየር እና ማውለቅ አይፈቀድም፡፡

     3. የችሎት አስከባሪ ፖሊስ ተገቢውን የደንብ ልብስ መልበስ አለበት፡፡

ችሎትን ስለማክበር

1. ማንኛውም የፍ/ቤቱ ሰራተኛ፣ ፖሊስ፣ የችሎቱ ተገልጋይ፣ ባለጉዳይ ወይም ተከራካሪ ወገን፣ ታዳሚ፣ ወይም በችሎት ውስጥ የተገኘ ማንኛውም ሰው ዳኛ ወደ ችሎት ሲገባና ሲወጣ እንዲሁም የማይስማማበት ቢሆንም ችሎቱ ትዕዛዝ፣ ብይን፣ ፍርድ፣ ውሳኔ ወይም ቅጣት አንብቦ ሲጨርስ ጉዳዩ የሚመለከተው ባለጉዳይ ራሱን ዘንበል በማድረግ ለችሎቱ  ክብር ማሳየት አለበት፡፡

ዳኞችን አክብሮ ስለመጥራት

1. የፍርድ ቤቱ ፕረዝዳንቶች እና አመራሮች ዳኞችን ክብርት ወይም ክቡር በማለት ተገቢውን ክብር ሰጥተው ንግግር ማድረግ አለባቸው፡፡

በግልፅ ችሎት ስለመዳኘት

1. በዝግ ችሎት እንዲታዩ በህግ ከተደነገጉ ጉዳዮች ውጪ ማንኛውም ጉዳይ በግልፅ ችሎት መካሄድ አለበት፡፡

የቀጠሮ አሰጣጥ

1. ዳኞች መዛግብትን በጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መቅጠር እና ማስተናገድ አለባቸው፡፡

ከዳኞች የሚጠበቅ ስነ-ምግባር

1. ዳኞች የእለቱ የችሎቱ መዛግብት መዘጋጀታቸውን ማረጋገጥ፣ እንደቅደም ተከተላቸው መለየት እንዲሁም ባለጉዳዮችም መዘጋጀታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

2. ዳኞች የችሎት ሰዓትን አክብረው ስራ መጀመር እና መዛግብትን በተቀጠሩበት ቀን እና ሰዓት ማስተናገድ አለባቸው፡፡ በበቂ ምክንያት ከዘገዩ ባለጉዳዮችን በማክበር ይቅርታ ይጠይቃሉ፡፡

 

ከባለጉዳዮች የሚጠበቅ ስነ-ምግባር

1. ባለጉዳዮች በቀጠሮው ቀን፣ ሰዓት እና ችሎት በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ዝግጅት አድርገው መገኘት አለባቸው፡፡

2. ባለጉዳዮች  ከላይ  በቁጥር  V-VIII  የተመለከቱትን  እና  የሚጠበቅባቸውን  የአክብሮት፣ የአነጋገር እንዲሁም የአለባበስ ስርዓቶች ማክበር፣ ማሟላት፣ መፈፀም እና በችሎት ውስጥ ተገቢውን የችሎቱን ስነምግባር መጠበቅ እና ማሳየት አለባቸው፡፡

ከሬጅስትራር እና ከፍርድ ቤቱ የአስተዳደር ሰራተኞች የሚጠበቅ ስነ- ምግባር

የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራሮች እና የአስተዳደር ሰራተኞች የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን እና ማሟላት አለባቸው፡፡

1. ለችሎቱ በቂ ድጋፍ የሚሰጡ የአስተዳደር ሰራተኞችን መመደብና በማንኛውም ሁኔታ ሲጓደል ችሎቱ ከመጀመሩ በፊት ማሟላት፡፡

ከቋንቋ አስተርጓሚ የሚጠበቅ ስነ- ምግባር

1. ቋንቋ የመተርጎም አገልግሎት በአግባቡ እና በትክክል ያለአድሎ ማካሄድ፡፡

2. ባለጉዳዮችን ማክበር እና በአግባቡ ማስተናገድ፡፡

ከችሎት ስነ-ስርዓት አስከባሪ የሚጠበቅ ስነ-ምግባር

1. ማንኛውም ሰው የችሎት ስነ-ስርዓት እንዲያከብር ማድረግ የችሎት ስነ-ስርዓት ተጥሶ ሲገኝ ለችሎቱ ዳኛ የማሳወቅ፡፡

2. በዳኛው የሚሰጠውን ትዕዛዝ ማክበር፣ መቀበል እና በአግባቡ መተግበር፡፡

ከችሎት ውጪና በችሎት አካባቢ የተከለከሉ ድርጊቶች

1. ለችሎቱ  ስራ  ሳያስፈልግ  ማንሾካሾክ፣  ማውራት፣  ድምፅ  ከፍ  በማድረግ  መናገር፣ መንጫጫት፣ ስልክ ማነጋገር፣

2. ጋዜጣ እና ማንኛውንም ሌሎች ፅሁፎችን ማንበብ፡፡

3. ሲጋራ ማጨስ፣ መጠጣት፣ መመገብ፣ መተኛት፡፡