የህጻናት ፍትህ ኘሮጀክት ጽ/ቤት
የህጻናት ፍትህ ኘሮጀክት ጽ/ቤት በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ የሚያልፉ የህጻናትን ጥቅምና ደህንነት ለማስጠበቅ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር የተቋቋመ ጽ/ቤት ነው፡፡ማዕከሉ ከ18 አመት በታች ለሆኑና በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ለሚያልፉ ህጻናት በሙሉ አገልግሎቱን ያለምንም ክፍያ በነፃ ይሰጣል፡፡
ማዕከሉ የሚሰጠው አገልግሎቶች
- የመክፈል አቅም ለሌላቸው ህጻናትና የህፃናቱን ጉዳይ ይዘው ለሚመጡ ባለጉዳዮች ነፃ የሕግ ድጋፍ መስጠት
- በፍርድ ቤትም ሆነ ከፍርድ ቤት ውጪ ለህፃናት መብትና ደህንነት መሟገት
- መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የማህበራዊና ስነልቦናዊ ድጋፍ መስጠት
- በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ከሚያልፉ ህፃናት ጋር በቅርብ ለሚሰሩ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት
- በፍ/ቤት ትዕዛዝ በመሰረት የዘረመል (DNA) ምርመራ እንዲካሄድ ድጋፍ መስጠት
- የማማከር አገልግሎት መስጠት
የሕግ ምክር አገልግሎት አይነቶች
- የቃል ምክክር
- አስፈላጊውን የፍርድ ቤት አቤቱታ፣ ማመልከቻና ቃለ መሐላ ማዘጋጀት
- የጥብቅና አገልግሎት መስጠት
- በባለሙያ የታገዘ የማስማማት አገልግሎት
- ለህግ አስፈፃሚ አካላት ተገቢውን የድጋፍ ደብዳቤና አቤቱታ መፃፍ
የማህበራዊና ስነልቦናዊ ድጋፎች
መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የማህበራዊና ስነልቦናዊ የሚሰጡበት አገልግሎት አይነቶች፤
- የምግብ፣የመጠለያ፣የትምህርት እና የትራንስፖርት ድጋፍ
- የስነልቦና ምክር
- የገቢ ማስገኛ ኘሮግራም
- ከቤተሰብ ጋር ማቀላቀል
አገልግሎቱ የሚሰጥባቸው ቦታዎች
- በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ኘሮጀክት ጽ/ቤት
- በፌዴራል ከፍተኛ ልደታ ምድብ ችሎት
- በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎቶች