የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት
ባለጉዳዮች በመረጡት የሕግ ጠበቃ የማቆም አቅም በማጣታቸው ፍትህ እንዳይጓደል ከመንግስት ጠበቃ የማግኘት መብት አላቸው፡፡
ተከላካይ ጠበቆች በወንጀል ተከሰው በገንዘብ እጥረት ምክንያት ጠበቃ ማቆም የማይችሉ እና ፍ/ቤት ጉዳዩ ያለ ጠበቃ ቢታይ የፍትህ መጓደል ይኖራል ብሎ ሲገምት በሚሰጠው ትዕዛዝ ወደ ጽ/ቤቱ ለሚመሩ ተከሳሾች አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 16 ንዑስ አንቀጽ 2/በ/ መሰረት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተደራጀ ሲሆን በወንጀል ተከሰው በፍርድ ቤት ጉዳያቸውን በራሳቸው ወጪ ጠበቃ ቀጥረው ለመከራከር ለማይችሉ ሰዎች ፍትህ እንዳይጓደል ነጻ የሕግ ድጋፍና ምክር አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስር የተዋቀረ ጽ/ቤት ነው፡፡
የተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት የሚሰጣቸው የአገልግሎት ዓይነቶች
- የማማከር አገልግሎት
- በችሎት ቀርቦ መከራከር
- ሰነድ የማዘጋጀት
- የማማከር አገልግሎት
- ተከሳሹ በፍርድ ቤት በኩል የዋስትና መብቱ ሲከበርለት በቂ ዋስ እንዲያቀርብ ማማከር፣
- የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ሚዛን ሲደፋ ክሱን አምኖ በቂ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት እንዲያቀርብ ማማከር፣
- የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ ከተከሳሾች ጋር በመመካከር ይግባኝ የማቅረብ ተግባር ማከናወን፤
- ተከሳሽ በማረሚያ ቤት ሆኖ እንዲከራከር ፍርድ ቤት ብይን ሲሰጥ ተከሳሹ ወደሚገኝበት ማረሚያ ቤት በመሄድ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ ፍርድ ቤት የዋስትና መብታቸው ለተጠበቀላቸው ተከሳሾች ደግሞ ለተከሳሹ ተገቢዉን የማማከር አገልግት እንድሰጥ በጽ/ቤቱ በተመራለት ተከላካይ ጠበቃ አማካይነት አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡
- በችሎት ቀርቦ መከራከር
- በሕጉ መሰረት የቀረበው ክስ የተከሳሾችን የዋስትና መብት የሚያስከለክል አይደለም ተብሎ ከታመነ ተከሳሾች የዋስ መብታቸው እንዲከበር መከራከር፤
- በችሎት ቀርቦ የክስ መቃወሚያ ማሰማት ወይም መከራከር፣
- ለዐቃቤ ሕግ ምስክሮች የመስቀለኛ ጥያቄ በማቅረብ ማስረጃ ማጥራት፣ ለተከሳሽ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ማሰባሰብ፣ በችሎት ቀርቦ ጭብጥ ማስያዝና መከራከር፤
- በቅጣት ውሳኔ ላይ የሕግ ስህተት ሲኖር ስልጣን ላለዉ ይግባኝ ሰሚ የፌደራል ፍርድ ቤት የይግባኝ አቤቱታ ወይም ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ ማቅረብ፤
- ሰነድ ማዘጋጀት
- ፍ/ቤቱ ተከሳሽ እንዲካላከል ብይን ሲሰጥ ሊያስተባብሉ የሚችሉ የሰውና የሰነድ የመከላከያ ማስረጃ ማዘጋጀት፣
- በጥፋተኝነት ወይም በቅጣት ውሳኔዎች እንዲሁም በሁለቱም ውሳኔዎች ላይ የይግባኝ ሰነድ ማዘጋጀትና ማቅረብ፣
- የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸውና የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ለሰበር የአቤቱታ ሰነድ ማዘጋጀት፣