የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት “ርትዕ “ መጽሄት ልዩ ዕትም ተሰራጨ፡፡

107

የ2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ3ኛው ስትራቴጂክ ዘመን መብቂያ እንደመሆኑ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከ 2014-2018 ዓ.ም የዓመስት ዓመት ቁልፍ ተግባራት ክንውን በልዩ ዕትም በመጽሄት በማሳተም እያሰራጨ ይገኛል፡፡

የዳኞች የስራ አፈፃፀም ምዘና ተጠናቀቀ።

105

የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መመሪያ ቁጥር 09/2015 መውጣቱን ተከትሎ ላለፉት አራት ዓመታት የዳኞች የስራ አፈፃፀም ምዘናን ሲያከናዉ መቆየቱ ይታወቃል ዘንድሮም የ2018 የስራ ዘመን (ከነሐሴ1 / 2017-ሐምሌ 30 /2018 ) ፍ/ቤቱ ባቋቋመው መዛኝ ኮሚቴ አማካኝነት ከሰኔ 12/2018 ጀምሮ ምዘናዉ ሲከናወን የቆየ ሲሆን እስከ ሐምሌ 30/2018 የዳኞች የችሎት ምልከታ እና መረጃ ሲሰባሰብ የቆየ ሲሆን በመመሪያው መሠረት ቀሪ ስራዎች ተከናውነው የተጠቃለለ ሪፖርት ለበላይ አመራሩ በዛሬው እለት በመዛኝ ኮሚቴዉ ቀርቧል፡፡

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ተሞክሮ በፍትህ ሚስንቴር በተዘጋጀ ወርክሾፕ ላይ ለተሳታፊዎች ቀረበ።

70

በፍትህ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተካሄደው የብሔራዊ አማራጭ አለመግባባት መፍቻ ዘዴዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናና ወርክሾፕ ላይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያካሄደውን የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ትግበራ በተመለከተ ለተሳታፊና ለባለድርሻ አካላት ተሞክሮውን እንዲያካፍል የቀረበለትን ጥያቄ ተከትሎ፣ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የፍርድ ቤቱን የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ተሞክሮ ለተሳታፊና ለባለድርሻ አካላት አቀረቡ።

የኢ-ፋይሊንግ ሲሰተም አተገባበር በሚመለከት ለሬጅሰትራሮ ሰልጠና ተሰጠ፡፡

105

የፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ አያየዝ በኩል ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀሰ (ለማዘዋወር) የሚባክነውን የሰው ጉልበት እና ጊዜን ለመቆጠብ የሚያሰችል የኢ-ፋይሊንግ ሲሰተም ትግበራ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሁሉም ምድብ ችሎቶች ሬጅሰትራሮች፣ የስካነር ባለሙያዎች እና ለአይ.ሲ.ቲ (ICT) ባለሙያዎች መሰከረም 7 እና 8 ቀን 2019 ዓ.ም ሰልጠና ተሰጠ፡፡

የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ስልጠና ለአመራሮች ተሰጠ።

267

በተሽከርካሪ ሥምሪት እና አጠቃቀም የሚባክነውን ሃብት ለመቆጣጠር የሚያስችል የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ትግበራ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለማስጀመር ለፍርድ ቤቱ የማኔጅመንት አባላት፣ የየምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኞች እና የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች ነሐሴ 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአምስት ዓመት (ከ2019 እስከ 2023) ረቂቅ ስትራቴጂያዊ እቅድ ላይ ውይይት ።

160

ፍርድ ቤት አስተባባሪነት ሲዘጋጅ የቆየው 4ኛው የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአምስት ዓመት (ከ2019 እስከ 2023) ረቂቅ ስትራቴጂያዊ እቅድ ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የማኔጅመንት አባላት፣ የምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኞች፣ አስተባባሪ ሬጅስትራሮች እና የስራ ክፍሎች ዳይሬክተሮች በተገኙበት ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ተደረገ።

የፌደራል ፍ/ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የስልጠና እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ።

241

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የስልጠና እቅድ በተመለከተ የተዘጋጀው የዳሰሳ ጥናት እና እቅድ ለፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የበላይ አመራሮች ቀርቦ ውይይት ተካሄደበት፡፡

የስልጠና እቅዱን ለበላይ አመራሮች ያቀረቡት የፌ/ጠ/ፍ/ቤት የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሮን ደጐል ሲሆኑ በጥናት ሠነዱ የ2018 የስልጠና እቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣የነበሩ ጠንካራ ጐኖች፣ክፍተቶች እና ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ የተካሄደበትን አግባብ እና የፍላጎት ዳሰሳ መሰረት በማድረግ የተለዩ 21 የስልጠና ርዕሶች እና ሰልጣኞች እቅድ አቅርበዋል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ ከቀረበ በኃላ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የበላይ አመራሮች በርከታ አስተያየት እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶል፡፡

አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሊያስከትል የሚችለዉን አተገባበርና ለውጥ በተመለከተ የጥናት ሠነድ ቀረበ !

157

አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 1410/18 መፅደቁን ተከትሎ በርካታ አዳዲስ አሠራሮች በአዋጁ የተካተቱ ከመሆኑም በላይ በርካታ የወንጀል ድንጋጌዎች ወደ ፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መውረዳቸዉ እና የአደረጃጀት እና አሠራር ለውጥ መካተቱ ይታወቃል፡፡

በመድን ሽፋን (Insurance Coverage ) ህግ እና አሰራር ላይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

217

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት (ነሐሴ 2 እና 3 ) የሚቆይ በመድን ሽፋን (Insurance Coverage ) ህግ እና አሰራር ላይ የታኮረ ስልጠና በቢሾፍቱ ከተማ እየሰጠ ይገኛል ።

በስልጠናዉ የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ሁሉም ዳኞች እና የምድብ ችሎቶች ተጠሪ ዳኞቸ የተገኙ ሲሆን ስልጠናዉ በዋናነት ከኢንሹራንስ ጋር የተያያዙ ህጎች እና አከራካሪ ጉዳዮች ላይ እየተሰጠ ነዉ ።

በድህረ-ውሳኔ መዛግብት ምርመራ እና በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁሉም ዳኞች ጋር ውይይት ተደረገ።

150

በድህረ-ውሳኔ መዛግብት ምርመራ እና በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ሁሉም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በተገኙበት ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በካፒታል አዲስ አበባ ሆቴል ውይይት ተደረገ።

1345678910Last