በመድን ሽፋን (Insurance Coverage ) ህግ እና አሰራር ላይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
/ Categories: News

በመድን ሽፋን (Insurance Coverage ) ህግ እና አሰራር ላይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር ጋር በመተባበር ለሁለት ቀናት (ነሐሴ 2 እና 3 ) የሚቆይ በመድን ሽፋን (Insurance Coverage ) ህግ እና አሰራር ላይ የታኮረ ስልጠና በቢሾፍቱ ከተማ እየሰጠ ይገኛል ።

በስልጠናዉ የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ሁሉም ዳኞች እና የምድብ ችሎቶች ተጠሪ ዳኞቸ የተገኙ ሲሆን ስልጠናዉ በዋናነት ከኢንሹራንስ ጋር የተያያዙ ህጎች እና አከራካሪ ጉዳዮች ላይ እየተሰጠ ነዉ ። በተለይም

-Insurance contract formation and related issues, Issue with Insurer's limit of liability under Insurance contract, Denial of liabllity (Defence raised by Insurers), Subrogation Suits and defense raised, Issue related with COMESA Treaty and Insurance related cassation decision ላይ በማተኮር እየተካሄደ ነው።

በመርሃ-ግብሩ መክፈቻ የኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ እመቤት አለማየሁ ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በሃገሪቱ የኢንሹራንስ ተቋማት እና አገልግሎት እየተስፋፋ መሆኑን በመግለፅ ስለ ኢንሹራንስ ስራው ተገቢ የሆነ ግንዛቤ ለመፍጠር ከዚህ በፊት ከፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ጋር የዚሁ አይነት የስልጠና መድረክ ተዘጋጅቶ ከተገኘው ግብአት እና ውጤታማነት በመነሳት እንዲሁም በፍርድ ቤቱ በኩልም በነበረ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

ክቡር አቶ ፋዓድ ኪያር የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በበኩላቸዉ የስልጠናውን አስፈላጊነት በዝርዝር በመግለፅ ዳኞች ከጠቅላላ የህግ እዉቀት በተጨማሪ ልዩ እዉቀት (specialized Knowledge ) በሚፈልጉ ጉዳዩች ላይ ተከታታይ ግንዛቤ ሊያገኙ እንደሚገባ ገልፀዋል ። በዚህም መርሃ-ግብሩን ላዘጋጁት የኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር እና ስልጠናው እንዲዘጋጅ ላስተባበሩት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኛ ክብርት ዳኛ ወይዘሮ ሮዛ አበበ ምስጋና አቅርበው ስልጠናውን ከፍተዋል። ስልጠናው በዘርፉ የካበተ ልምድ ባላቸው አቶ ፈቃዱ ያሚ እና አቶ ጌቱ መልኬ አማካኝነት እየተሰጠ ይገኛል።

Previous Article በድህረ-ውሳኔ መዛግብት ምርመራ እና በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁሉም ዳኞች ጋር ውይይት ተደረገ።
Next Article አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሊያስከትል የሚችለዉን አተገባበርና ለውጥ በተመለከተ የጥናት ሠነድ ቀረበ !
Print
698