አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሊያስከትል የሚችለዉን አተገባበርና ለውጥ በተመለከተ የጥናት ሠነድ ቀረበ !
/ Categories: News

አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሊያስከትል የሚችለዉን አተገባበርና ለውጥ በተመለከተ የጥናት ሠነድ ቀረበ !

አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 1410/18 መፅደቁን ተከትሎ በርካታ አዳዲስ አሠራሮች በአዋጁ የተካተቱ ከመሆኑም በላይ በርካታ የወንጀል ድንጋጌዎች ወደ ፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መውረዳቸዉ እና የአደረጃጀት እና አሠራር ለውጥ መካተቱ ይታወቃል፡፡

ይህን ተከትሎ አዲሡ አዋጅ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የሚኖረውን / ሊያስከትል የሚችለውን የአደረጃጀት እና አተገባበር ለውጥ በተመለከተ ጥናት አጥንቶ የሚያቀርብ 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በማዋቀር ወደ ስራ የተገባ ሲሆን በዚህ መሠረት የተዋቀረው ኮሚቴ የጥናት ሠነዱን የመጀመሪያ ረቂቅ ለፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት የበላይ አመራር (ማኔጅመንት) አቅርቧል፡፡

ጥናት ሰነዱ ያቀረብት የኮሚቴው ሰብሳቢ እና አባላት ሲሆኑ የጥናት ሠነዱ ከቀረበ ቡሃላ በርካታ አስተያየቶች ተነስተው ሊጨመር፣ሊቀነስ፣እና ሊሻሻል ይገባሉ በተባሉት ጉዳዬች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም ሠነዱ በተሰጡት አስተያየቶች እንዲዳብር እና የመጨረሻ ይዘቱን ከያዘ ቡሃላ ለትግበራ ስራ ለበላይ አመራሮች የሚቀርብ ይሆናል፡፡

 

Previous Article በመድን ሽፋን (Insurance Coverage ) ህግ እና አሰራር ላይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
Next Article የፌደራል ፍ/ቤቶች የአስተዳደር ሠራተኞች የ2019 በጀት ዓመት የስልጠና እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ።
Print
433