የኢ-ፋይሊንግ ሲሰተም አተገባበር በሚመለከት ለሬጅሰትራሮ ሰልጠና ተሰጠ፡፡
የፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ አያየዝ በኩል ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀሰ (ለማዘዋወር) የሚባክነውን የሰው ጉልበት እና ጊዜን ለመቆጠብ የሚያሰችል የኢ-ፋይሊንግ ሲሰተም ትግበራ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሁሉም ምድብ ችሎቶች ሬጅሰትራሮች፣ የስካነር ባለሙያዎች እና ለአይ.ሲ.ቲ (ICT) ባለሙያዎች መሰከረም 7 እና 8 ቀን 2019 ዓ.ም ሰልጠና ተሰጠ፡፡
በስልጠናው መክፈቻ የፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍረድ ቤቱን የደኝነት አገልግሎቱ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ ከማድረግ አንፃር በመዝገብ አያያዝ በኩል ፍርድ ቤቱ የተገልጋዩንም ሆነ የአገልጋዩን ጊዜ ለመቆጠብ እንዲሁም የመዝገብ ከቦታ ቦታ ይዞ መንቀሳቀሰን ለማስቀረት ዘመናዊ የሆነውን የኢ-ፋይሊንግ ሲስተም አሰራር ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን ባለሙያዎች በይበልጥ በእውቀት ላይ ተመስርተው የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰጡ በኢ-ፋይሊንግ ሲስተም ላይ ግንዛቤያቸውን ለማሳደግ ስልጠናው መዘጋጀቱን በመግለፅ ትኩራት ሰጥተው እንዲከታተሉት የፍርድ ቤቱ ዋና ሬጅሰትራር ወ/ሮ ፈትለወርቅ አንዳርጌ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የኢንፎርሜሸን ኮምንኬሸን ቴከኖሎጂ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ፍፁም ታምራት ሲሆኑ ሲስተሙ ፍርድ ቤቱን ወደ ዘመናዊ፣ ዲጂታል እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጋ ከመርዳቱ በተጨማሪ የኢ-ፋይሊንግ ሲስተምን መጠቀም ግልፅ እና ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት ለማግኘት፣ የወረቀት ስራዎችን ለማስቀረት፣ ከሰዎች ንኪኪ ነፃ የሆነ አሰራር ስርዓት ለመዘርጋት፣ የተጠቃሚዎች ጊዜን ለመቆጠብ እንዲሁም ቀልጣፋ እና ግልፅ የመዝገብ አያያዝ ወይም መዝገብ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ለመላክ የሚያሰችል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
639