የዳኞች የስራ አፈፃፀም ምዘና ተጠናቀቀ።
የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መመሪያ ቁጥር 09/2015 መውጣቱን ተከትሎ ላለፉት አራት ዓመታት የዳኞች የስራ አፈፃፀም ምዘናን ሲያከናዉ መቆየቱ ይታወቃል ዘንድሮም የ2018 የስራ ዘመን (ከነሐሴ1 / 2017-ሐምሌ 30 /2018 ) ፍ/ቤቱ ባቋቋመው መዛኝ ኮሚቴ አማካኝነት ከሰኔ 12/2018 ጀምሮ ምዘናዉ ሲከናወን የቆየ ሲሆን እስከ ሐምሌ 30/2018 የዳኞች የችሎት ምልከታ እና መረጃ ሲሰባሰብ የቆየ ሲሆን በመመሪያው መሠረት ቀሪ ስራዎች ተከናውነው የተጠቃለለ ሪፖርት ለበላይ አመራሩ በዛሬው እለት በመዛኝ ኮሚቴዉ ቀርቧል፡፡
በዚህም በ2018 የስራ ዘመን አዲስ የተሾሙ እና በወሊድ እረፍት ምክንያት በስራ ላይ ያልተገኙ ዳኞች ያልተመዘኑ ሲሆን ቀሪ 130 ዳኞች በምዘና ሂደቱ ያለፉ ሲሆን ከፍተኛ ውጤት 99.66% ዝቅተኛው ደግሞ 80.63% ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን አማካይ ውጤቱ 90.8% ሊሆን ችሏል፡፡
በምዘና ሂደቱ ለ1 ዳኛ 12 ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ቅፅ የተሞላ ሲሆን የፍ/ቤቱ ተገልጋዮች፣ጠበቆች፣ዓቃቢያን ሕጐች፣የከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች፣የዳኞች የስራ ባልደረቦች፣የጉባኤ ተሿሚዎች፣የአስተዳደር ሰራተኞች፣ተጠሪ ዳኞች፣የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት እና የፍ/ቤቱ ኘሬዝዳንት ተሳትፈዋል፡፡
የተጠቃለለ ሪፖርት እና ውጤት በመመሪያው መሠረት በቀጣይ ለእያንዳንዱ ዳኛ በፍ/ቤቱ ኘሬዝዳንት በኩል የሚገለፅ ሲሆን ዝርዝር ሪፖርቱም ለዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሚላክ ይሆናል፡፡
599