የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ተሞክሮ በፍትህ ሚስንቴር በተዘጋጀ ወርክሾፕ ላይ ለተሳታፊዎች ቀረበ።
በፍትህ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተካሄደው የብሔራዊ አማራጭ አለመግባባት መፍቻ ዘዴዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናና ወርክሾፕ ላይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያካሄደውን የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ትግበራ በተመለከተ ለተሳታፊና ለባለድርሻ አካላት ተሞክሮውን እንዲያካፍል የቀረበለትን ጥያቄ ተከትሎ፣ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የፍርድ ቤቱን የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ተሞክሮ ለተሳታፊና ለባለድርሻ አካላት አቀረቡ።
በመድረኩ ፍርድ ቤቱ በ2010 ዓ.ም የመጣውን ሀገራዊ የፖለቲካ አመራር ለውጥ ተመርኩዞ ፍርድ ቤቶችን ለማዘመንና ቀልጣፋ የፍትህ አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ የፍርድ ቤት መር አስማሚነትን መጀመሩ ተገልጿል።
በፍርድ ቤቱ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ስራ በሁለት ዋና ዋና ምዕራፎች፣ በመጀመሪያ ምዕራፍ በሙከራ ትግበራ እና በቀጣይ ምዕራፍ በሙሉ ትግበራ የተከናወነ ሲሆን፣ በነዚህ የትግበራና የተሞክሮ ሂደቶች የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎች፣ የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም ወደፊት ትኩረት ተሰጥቶ መፍትሔ ሊሰጣቸው የሚገቡ ክፍተቶች በመድረኩ ቀርበዋል።
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በህግ አግባብ ለሌሎች የአማራጭ አለመግባባት መፍቻ ዘዴዎች፣ የግልግል ዳኝነትን ጨምሮ፣ ድጋፍ ሊያደርግ በሚችልባቸው ሂደቶች ላይ ከጉባኤው በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ወክለው በወርክሾፑ ላይ በተገኙ ማብራሪያዎችና አስተያየቶች ተሰጥተዋል።
469