202
በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና በፌደራል ህግና ፍትህ ኢንስቲትዩት ትብብር ለፍርድ ቤቱ ረዳት ዳኞች እና አስማሚ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ክህሎት ማበልፀጊያ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
113
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የ6ኛዉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ፅ/ቤት ሀላፊ እና አባላት፥ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ÷ የፌደራል የማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ÷ የኢትዬዽያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር : የፌደራል ሕግ እና ፍትህ ኢንስትትዮት ም/ዋና ዳይሬክተር : የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ም/ ሀላፊ : የፌደራል የጠበቆች ማህበር ፕሬዚደንት ÷ ክቡራን ተጠሪ ዳኞች፣ ክቡራን ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ረዳት ዳኞች በተገኙበት በኃይሌ ግራንድ አዲስ ሆቴል ተካሂዶል።
71
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ ክቡራን ዳኞች፣ ረዳት ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ የምድብ ችሎቱ ሰራተኞች በተገኙበት በድሬዳዋ ከተማ የምድብ ችሎቱ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት እና የእውቅና እና ሽልማት መርሃግብር ተከናወነ። መርሃግብሩን በእንኳን ደህና ቆያችሁን እና በመክፈቻ ንግግራቸው የከፈቱት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ የአስተዳደር እና ሰው ሃብት ልማት ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር ዳኛ የምስራች ከተማ ሲሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት እና የስትራቴጂክ ዘመኑ ማጠቃለያ ስኬታማ ስራዎችን መስራቱን ለዚህም ውጤታማ የዳኝነት አገልግሎት መሰጠቱን፣ ከታቀደው በላይ መዝገቦች በውስን ዳኞች መፈፀማቸው፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኢ-ፋይሊንግ፣ ድምፅን ወደ ፅሁፍ የመቀየር እና የስካኒንግ... ወዘተ አገልግሎቶች ተግባራዊ መደረጋቸው፣ ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ችሎቶችን ተደራሽ እና ለአገልግሎት ምቹ የማድረግ፣ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ለመገንባት ሁኔታዎች መመቻቸታቸው፣ አጠቃላይ አፈፃፀም በመገምገም ለዳኞች እና ለሰራተኞች እውቅና እና ሽልማት መሰጠቱ፣ ከተመደበው በጀት 99.9 በመቶ በስራ ላይ መዋሉ፣ ስልጠና ለዳኞች እና ሰራተኞች መሰጠቱ፣ የመዝገቦች ድህረ ኦዲት መከናወኑ፣ በጥፋት የተገኙ ዳኞች እና ሰራተኞች ተጠያቂ መሆናቸው በጥንካሬ ያነሱ ሲሆን ለዚህም የፍርድ ቤቱ ክቡራን ዳኞች፣ ተጠሪ ዳኞች፣ የጉባኤ ተሿሚዎች እና የፍርድ ቤቱ ሰራተኞች ለነበራቸው አስተዋፅኦ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ በጀት ዓመት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን በጥበቅ መተግበር፣ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ይበልጥ ማከናወን፣ የተገልጋይ እርካታ ጥናት በውስንነት በተነሱ በዳኝነት ጥራት፣ በስነምግባር እና በተገማችነት ላይ እየተነሱ የሚገኙ ቅሬታዎች መቀነስ ላይ ትኩረት ማድረግ የሚገባ መሆኑን አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
178
የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ሰራተኞች ዓመታዊ በዓል እና የችሎት መክፈቻ ከአንድ ሺህ በላይ ሰራተኞች፥ ክቡር የፍ/በቱ ፕሬዝዳንት ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሠው ሀብት ስራ አመራር ጉባዔ አባላት ክብርት ወ/ሮ ከዲጃ ያሲን እና ክቡር ዶ/ር ከበደ ገነቴ÷ ተጠሪ ዳኞች ፣ አስተባባሪ ሬጅስትራሮች ፣ ዳይሬክተሮች ÷ ሬጅስትራሮች እና የስራ ክፍል ኃላፊዋች በተገኙበት በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋና መስሪያ ቤት ግቢ መስከረም 30 /2019 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል።
231
አዲሱ የወንጀል ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 1410/18 መፅደቁን ተከትሎ በርካታ አዳዲስ አሠራሮች በአዋጁ የተካተቱ ከመሆኑም በላይ በርካታ የወንጀል ድንጋጌዎች ወደ ፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መውረዳቸዉ እና የአደረጃጀት እና አሠራር ለውጥ መካተቱ ይታወቃል፡፡
514
የ2018 ዓ.ም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ3ኛው ስትራቴጂክ ዘመን መብቂያ እንደመሆኑ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከ 2014-2018 ዓ.ም የዓመስት ዓመት ቁልፍ ተግባራት ክንውን በልዩ ዕትም በመጽሄት በማሳተም እያሰራጨ ይገኛል፡፡
597
የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት መመሪያ ቁጥር 09/2015 መውጣቱን ተከትሎ ላለፉት አራት ዓመታት የዳኞች የስራ አፈፃፀም ምዘናን ሲያከናዉ መቆየቱ ይታወቃል ዘንድሮም የ2018 የስራ ዘመን (ከነሐሴ1 / 2017-ሐምሌ 30 /2018 ) ፍ/ቤቱ ባቋቋመው መዛኝ ኮሚቴ አማካኝነት ከሰኔ 12/2018 ጀምሮ ምዘናዉ ሲከናወን የቆየ ሲሆን እስከ ሐምሌ 30/2018 የዳኞች የችሎት ምልከታ እና መረጃ ሲሰባሰብ የቆየ ሲሆን በመመሪያው መሠረት ቀሪ ስራዎች ተከናውነው የተጠቃለለ ሪፖርት ለበላይ አመራሩ በዛሬው እለት በመዛኝ ኮሚቴዉ ቀርቧል፡፡
470
በፍትህ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተካሄደው የብሔራዊ አማራጭ አለመግባባት መፍቻ ዘዴዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናና ወርክሾፕ ላይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያካሄደውን የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ትግበራ በተመለከተ ለተሳታፊና ለባለድርሻ አካላት ተሞክሮውን እንዲያካፍል የቀረበለትን ጥያቄ ተከትሎ፣ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የፍርድ ቤቱን የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ተሞክሮ ለተሳታፊና ለባለድርሻ አካላት አቀረቡ።
637
የፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ አያየዝ በኩል ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀሰ (ለማዘዋወር) የሚባክነውን የሰው ጉልበት እና ጊዜን ለመቆጠብ የሚያሰችል የኢ-ፋይሊንግ ሲሰተም ትግበራ በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሁሉም ምድብ ችሎቶች ሬጅሰትራሮች፣ የስካነር ባለሙያዎች እና ለአይ.ሲ.ቲ (ICT) ባለሙያዎች መሰከረም 7 እና 8 ቀን 2019 ዓ.ም ሰልጠና ተሰጠ፡፡
888
በተሽከርካሪ ሥምሪት እና አጠቃቀም የሚባክነውን ሃብት ለመቆጣጠር የሚያስችል የኢ-ፍሊት ማኔጅመንት ትግበራ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለማስጀመር ለፍርድ ቤቱ የማኔጅመንት አባላት፣ የየምድብ ችሎት ተጠሪ ዳኞች እና የስራ ክፍል ዳይሬክተሮች ነሐሴ 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።