የሬጅስትራሮች አቅም ግንባታ

911

የፌደሬል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚሰሩ ሬጅስትራሮች ሹመት ሰጥቷል፡፡ በዚሁ መሰረት አዲስ የተሾሙ ሬጅስትራሮች የፍርድ ቤቱን ራዕይ እና ተልእኮ በብቃት መወጣት እንዲችሉ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የአስተዳደር ሰራተኞቸ እና ኃላፊዎች ስልጠና

939

በሶስቱም የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከደረጃ 11 በላይ ለሚገኙ ሰራተኞች የፌዴራል አስተዳደር ሰራተኞች ደንብ፣ አዲስ በወጡ የሰው ሀብት ስራ አመራር መመሪያዎች፣ ተቋማዊ ለውጥ፣ የስራ ባህል እና ስነ ምግባር፣ አዲሱ የህዝብ አገልግሎት አቀራረብ ስልት ለተሻለ ተቋማዊ አፈጻጸም እና የዲጂታላይዜሽን ጉዞ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች በሚሉ ርዕሶች ላይ በተለያዩ ዙሮች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኀበር ድጋፍ ተደረገ

1098

በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር የተመራ የፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ተጠሪ ዳኞች፣ የስራ ክፍል ሃላፊዎች የፍርድ ቤቱን ዳኞች፣ የጉባኤ ተሻሚዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ድርጅት ያዋጡትን የገንዘብ ድጋፍ ለማህበሩ መስራች ለሆኑት ለክቡር ዶ/ር ቢኒያም በለጠ አበረከቱ፡፡

የውርስ ችሎት የዳኞች ፎረም ውይይት ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

982

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች እርስ በርሳቸው ልምድና ክህሎት የሚለዋወጡበት፣ በዳኞች መካከል ያለዉን የህግ አተጓጐም እና አሰራር የተቀራረበ እና ተገማች እንዲሆን ለማድረግ በጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ እና ማኑዋል መሠረት በጉዳዮች ዓይነት የተለያዩ የዳኞች ፎረሞችን በማደራጀት ከፍተኛ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

በሀረር ከተማ የስራ እና የተለያዩ ቦታዎች ጉብኝት ተደረገ፡፡

1032

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች ፣ ተጠሪ ዳኞች፣ ዳኞች፣ ዳይሬክተሮች የመቻቻል እና የፍቅር ከተማ በሆነችው በሀረር ከተማ በመገኘት በሀረር ከተማ ውስጥ የሚገኙ ከ1300 ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ የተለያዩ የታሪክ እና የስልጣኔ ምስክር የሆኑ ቅርሶችን እና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትን ጎብኝተዋል፡፡ ሀረር ሀገራችን የብዙ ዘመናት ታሪክ እና ስልጣኔ ባለቤት መሆናን ከሚያመለክቱ ቦታዎች አንዱ ሲሆን ጉብኝቱም ስለ ሀረር በቂ ግንዛቤ ለመያዝ የሚያስችል እድል የፈጠረ ነው፡፡

የዳኞች መኖሪያ ቤት ርክክብ እና የድሬዳዋ ምድብ ችሎት የስራ ጉብኝት ተካሄደ::

892

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ፋዓድ ኪያር÷ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ÷ ተጠሪ ዳኞች እንዲሁም ዳይሬክተሮች በተገኙበት የድሬዳዋ ምድብ ችሎት የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ የስራ ጉብኝት የተከናወነ ሲሆን በመቀጠልም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎት ተመድበው የዳኝነት አገልግሎት ለሚሰጡ ክቡራን ዳኞች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በልዮ ሁኔታ ያለ ዕጣ የተሰጡ እና በፍርድ ቤት ሙሉ ክፍያ እና እድሳት የተደረገባቸው የዳኞች መኖሪያ ቤቶች የድሬዳዋ አስተዳደር የቤቶች ልማት እና የኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ ክቡር ኢንጅነር አቶ ዑመር ዱአሌ በተገኙበት የርክክብ መርሀ ግብር ተከናውኗል::

የ2017 የ6ወር የዕቅድ አፈፃፀም ውይይት መድረክ በድሬዳዋ ተካሄደ፡፡

1213

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች÷ የሁሉም ምድብ ችሎቶች ተጠሪ ዳኞች፣ ዳይሬክተሮች እና ሬጅስትራሮች በተገኙበት የፍርድ ቤቱ የ2017 በጀት የ6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በድሬዳዋ ተካሂዷል።

አዲስ ለተሾሙ ሬጂስትራሮች የትውውቅና የስራ ገለጻ ተደረገ ፡፡

167

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አዲስ ለሾማቸው ከ42 በላይ ለሚሆኑ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሬጂስትራሮች የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ፤ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሚመለከታቸው የስራ ክፍል ሃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ማለትም ጥር 08/2017 ዓ.ም በፍርድ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ የስራ ገለጻ ተደርጓል፡፡

ሀገር አቀፍ የዳኝነትና የፍትሕ አካላት የምክክር መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

861

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶችና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፣ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትርና ሚኒስትር ዲኤታዎች፣ የፌዴራል ፣ የክልልና የከተማ መስተዳደሮች የዳኝነት አካላት እና የፍትሕ አካላት አመራሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጉዲፈቻ እና ፍቺ ውሳኔ ምዝገባ ዛሬ ተጀመረ

1172

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚወሰኑ የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎችን የመመዝገብ አገልግሎት በአንድ ማዕከል ለመስጠት የሚያስችለውን የስራ ስምምነት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር በፈፀመው መሰረት ዛሬ ታህሳስ 9/2017 ዓ.ም በይፋ አገልግሎቱ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአራዳ÷ የካ እና ቦሌ ምድብ ችሎቶች ተጀምሯል።

First3456781012