ኢ-ፋይሊንግ (e-Filing) ስራ ለመጀመር የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ

995

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት ቀልጣፋ፣ ዘመናዊ እና ተደራሽ ለማድረግ በርካታ የለውጥ ስራዎች እየሰሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከለውጥ ስራዎች መካከል የዲጂታይዘሽን ስራ ይገኝበታል፡፡ መዝገቦችን እስካን በማድረግ ወደ ዲጅታል የመዝገብ ዓይነት የመቀየር ስራ በአራት ምድብ ችሎቶች በልደታ፣ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎቶች ከመስከረም 2018ዓ/ም ጀምሮ እየተሰራበት የቆየ ሲሆን ወደ ዲጅታል የመዝገብ ዓይነት የተቀየሩ ይግባኝ የሚጠየቅባቸው መዝገቦች ወደ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚላክበት የኢ-ፋይሊን ሲስተም Electronic Filing (e-Filing System) ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለመላክ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል፡፡

አለም አቀፍ ንግድ : የባንክ ዎስትና እና የዲጂታል ባንኪንግ ጋር በተያያዙ ጉዳዬች ላይ ስልጠና መስጠት ተጀመረ ።

163

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር በ "International Trade, Bank Gurantee እንዲሁም በ Digital Banking" ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ለፍርድ ቤቱ አመራሮች፣ ለ13ቱም ምድብ ችሎት ድሬደዋን ጨምሮ ተጠሪ ዳኞች እንዲሁም ለዳኞች መጋቢት 18 እና 19 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁለት ቀን የሚቆይ በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው መክፈቻ ወ/ሮ ሶስና አለማየሁ የህግ አገልግሎት ዲቪዥን ም/ፕሬዝዳንት ባስተላለፋት መልእክት ንግድ ባንኩ ስራ ላይ ስላዋላቸው የዲጂታል አማራጮች፣ ስለ ህግ ማእቀፎች፣ በዲጂታል የፋይናንስ እንቅስቃሴ ውስጥ ስለሚታዩ የፍትሀብሔር እና የወንጀል ተጠያቂነትን እንዲሁም ባንኮች የሚመሩባቸውን ህግጋቶች ለማሳወቅ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ

768

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር በ "International Trade, Bank Gurantee እንዲሁም በ Digital Banking" ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ለፍርድ ቤቱ አመራሮች፣ ለ13ቱም ምድብ ችሎት ድሬደዋን ጨምሮ ተጠሪ ዳኞች እንዲሁም ለዳኞች መጋቢት 18 እና 19 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ።

ሀገር አቀፍ የዳኝነት እና የፍትህ አካላት የጋራ መድረክ ተጠናቀቀ

802

‎አዲስ አበባ፦ መጋቢት 19/2018 ዓ/ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት)

‎

‎ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው አመታዊ ሀገር አቀፍ የዳኝነት እና የፍትህ አካላት የጋራ የምክክር መድረክ (ጆይንድ አፕ ጀስቲስ ፎረም) የፌዴራልና የክልል የዳኝነትና የፍትህ አካላት የጋራ መድረክ የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ስነ ስርዓት በማከናወን ተጠናቋል።

‎

‎የመግባቢያ ሰነዱ የዳኝነትና የፍትህ አካላት የዕቅድ አፈጻጸም በጋራና በትብብር የሚታይበት ስርዓት መዘርጋት፣ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮች ላይ የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥና የተሳለጠ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ትኩረቱን በባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ላይ ያደረገ አህጉራዊ ኮንፍረንስ በመዲናችን አዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ መካሄድ ጀመረ

406

ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀውና ባሕላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች በፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ያላቸው ሚናና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው አህጉራዊ ኮንፍረንስ “Strengthening Traditional Dispute Resolution For Access To Justice In Africa” በሚል ርዕስ በመዲናችን አዲስ አበባ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም መጋቢት 16/2018 ዓ.ም መካሄድ ጀምሯል።

የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች በሚኖራቸው የሁለት ቀን ቆይታ በአህጉሪቱ በሚገኙ ባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች ላይ በጋራ ይወያያሉ፣ ዕርስ በርሳቸው ካላቸው ልምድ ይማማራሉ እንዲሁም ትብብሮችን ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል፡፡

የተጠሪ ዳኞች ፎረም !!

951

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁሉም ምድብ ችሎት ለሚገኙ ተጠሪ ዳኞች መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ∙ም በፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የፎረም ዉይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር ተከናወነ።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብሩ የተገኙት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር ተጠሪ ዳኞች በየምድብ ችሎቶቻቸው ተቀራራቢ የሆነ አሰራር ለመፍጠር መድረኩ ልምድ የምትለዋወጡበት በመሆኑ በቀጣይነት ጠንክሮ መገናኘት እና መስራት እንደሚገባ በማሳሰብ በተለይ አዲስ ተሿሚ ዳኞችም ሆኑ ሌሎች የፍርድ ቤቱ ባለሙያዎች እና ሰራተኞችን በተሻለ ስነ-ምግባር እና በጥብቅ ዲሲፒሊን ወደ ስራ ማስገባት፣ መከታተል እና መደገፍ እንዲሁም በየምድብ ችሎቱ ባልተከናወኑ ተግባራት ላይ ትኩረት አድርጎ ለተሻለ አፈፃፀም መስራት እንደሚገባ ለዚህም የየምድቡ ተጠሪ ዳኞች ተፅእኖ ፈጣሪ መሆን እንደሚገባቸው እና የተግባቦት /የኮሙኒኬሽን/ ክህሎታቸውን ማዳበር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ የተከበሩ አቶ ፉዓድ ኪያር በየምድብ ችሎቶች ለአስተማሪነት የሚሆኑ መገለጫዎችን በማንሳት በተለይ ከስነ-ምግባር ጋር ተያይዞ በአቤቱታ የሚገለፁ ከመዝገቦች መሰወር፣ ከባለ ጉዳዮች መስተንግዶ ጉድለት፣ ከግልፅ ችሎት ወደኋላ የመመለስ ጅምሮች፣ በሰዓት በአግባቡ አለመጠቀም፣ ሚዛናዊ ሆኖ ነገሮችን ሳይጋነንም እንዲሁም ሳያንስም በልኩ በማየት ተከታትሎ መስራት እንደሚገባ በመርሃ-ግብሩ መክፈቻ መልዕክታቸው አሳስበዋል።`

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አለም አቀፉን የሴቶች ቀን አከበሩ

1156

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዘንድሮ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ማርች 8 በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ GIVE TO GAIN በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ "የሴቶች ድምጽ ለዕኩልነት እና ለበለጸገች ኢትዮጵያ "በሚል መሪ ቃል መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተከብሯል፡፡

በመሰረታዊ የቤተሰብ ህግ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረክ ተካሄደ

1006

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት÷ከJustice for All-PF Ethiopia (JFA-PFE)፣ ከቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ቢሮ (OFCJ-MA) እንዲሁም ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለኤጀንሲው ሀላፊዎች እንዲሁም ሰራተኞች በመሰረታዊ የቤተሰብ ህግ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማሳደጊያ መድረክ ተካሂዷል።

12ኛዉ ልዩ የሴቶችና ህፃናት ችሎት በአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎት !!!

1324

ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 12ኛዉ ልዩ የሴቶችና ህፃናት ልዩ ችሎት በአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎት የስራ ማስጀመሪያ መርሃግብር የፍርድ ቤቱ ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ፎዓድ ኪያር÷ የፍትህ ለሁሉም (Justice for all) ፕሬዚደንት ፓስተር ዳንኤል ገ/ስላሴ÷ የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ÷ የስራ ሀላፊዎች÷ ዳኞችና የምድብ ችሎቱ ሰራተኞች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን ልዩ የሴቶች እና ህፃናት ችሎት የተደራጀው በፍትህ ለሁሉም (Justice for all) በተደረገ ሙሉ ድጋፍ ነዉ::

በመርሀ ግብሩ አገልግሎት አሰጣጡን በተመለከተ ገለፃ ÷ የችሎት ምልከታ እንዲሁም ጉብኝት እና ውይይት ተደርጓል።

በፍትሃ-ብሄር የስነ-ስርዓት ህግ ላይ አዲስ ለተሾሙ ዳኞች ስልጠና ተሰጠ።

96

ሁለተኛ ቀን በያዘው የስልጠና መርሃግብር ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ የተሾሙ ዳኞች በስነ-ስርዓት ህግ ዙሪያ ፣ ህጉ፣ አተገባበሩ ፣ በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እና የሰበር ውሳኔዎችን ያካተተ ስልጠና ተሰጥቷል ።

124678910Last