አዲስ ለተሾሙ ዳኞች አቀባበልና ትዉዉቅ ተደረገ፡፡

1219

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት በዛሬዉ እለት ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባ 23 ሴት እጩዎችንና 27 ወንድ እጩዎችን በድምሩ 50 የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል፡፡

በድሬደዋ ምድብ ችሎት ጉብኝት እና የ6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ።

1524

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም በድሬደዋ ከምድብ ችሎቱ ዳኞች፣ የክፍል ኃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎች እና ሁሉም<

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለዋና መስሪያ ቤት አዲስ በሚያሰራው ህንፃ ዲዛይን ላይ ከባለ ድርሻ አካለት ጋር ምክክር ተደረገ።

500

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም በኢፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ ዘርፍ የልደታ ቅርንጫፍ ለፅህፈት ቤት በአዲስ የሚገነቡ ህንፃዎች ዲዛይንን አስመልክቶ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ጥር 23 ቀን 2018 ዓ∙ም በካፒታል ሆቴል ምክክር ተደረገ።

አዲስ ለተቀጠሩ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

1065

የፌዴራል መጀመረያ ደረጀ ፍርድ ቤት የጀመረዉን የሪፎርም ስራ ለማሳለጥ እና የዳኝነት አገልግሎቱን ለማሻሻል አዲስ በተጠናው የሰው ሃይል መዋቅር መሰረት በርካታ የሰው ኃይል እየቀጠረ ይገኛል። በዚሁ መሰረት ባለፉት ስድስት ወራት ፍርድ ቤቱን የተቀላቀሉ ከአንደ መቶ ዘጠና በላይ ለሚሆኑ እና በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለተቀጠሩ ሰራተኞች አጠቃላይ የፌደራል ፍርድ ቤቶችን አደረጃጀት እና አሰራር እና ህጎች እንዲሁም ሰራተኞች ሊላበሱ ስለሚገባቸው ሙያዊ ስነ-ምግባርን በተመለከተ በፍርድ ቤቱ የመሰብሰቢያ አደራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

የ6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ።

953

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር፣ ምክትል ፕሬዚዳንት አሸነፈች አበበ÷ የሁሉም ምድብ ችሎቶች ተጠሪ ዳኞች÷ ዳይሬክተሮች÷ አስተባባሪ ሬጅስትራሮች እና የዳኞች ፎረም ሰብሳቢዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል::

የመርሀ ግብሩን መክፈቻ ያደረጉት የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዚደንት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ ሲሆኑ በ6ወራት በየምድቡና በየዳይሬክቶሬቱ ተገምግሞ ከቀረበው ከመዝገብ አፈፃፀም÷

የፍትሀብሄር ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያ በጥብቅ ከመተግበር በተለይም ከጊዜ ገደብ በተጨማሪ ግልፅ ችሎት ማስተናገድ÷ ቅድሚያ ትኩረት የሚሹ ተገልጋዮች[ነፍሰጡር÷ ህፃናት÷ አረጋዉያን÷ አካል ጉዳተኞች÷ ቅድሚያ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች(ዕግድ÷ እስረኛ ያላቸዉ÷ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸዉ÷ ቀለብ..]÷ ችሎት ሰዓት÷ ስነምግባር ክትትል÷ አስማሚነት ÷ የሬጅስትራር አገልግሎት አሰጣጥ÷ ከጥንታዊ ስራዎች÷ የባለሙያዎች አቅም ከመገንባት አንፃር በርካታ የዳኝነት እና አስተዳደራዊ ተግባራት በዉስን የሰዉ ሀይል በጀት መከናወኑ ይህም ጥንካሬ በበለጠ ቁርጠኝነት ሊጠናከር እንደሚገባ ዉስንነቶች ላይ በቀጣይ ወራት በበለጠ መረባረብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል::

ሰብዓዊ መብት ከማስከበር አንፃር የዳኞች ሚና በተመለከተ የምክክር መድረክ ተካሄደ::

694

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከኢትዮጲያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን ሰብዓዊ መብት ከማስከበር በተለይም ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች እና ህፃናት መብቶች ከማስከበር አንፃር የዳኞች ሚና በተመለከተ ያሉ መልካም ተሞክሮዎች በዋናነትም በህግ አተገባበር÷ በአሰራር መሻሻል ባለባቸዉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የምክክር መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ ለቤተሰብ ችሎት እና በሴቶች እና ህፃናት ልዩ ችሎት ለሚሰሩ ክቡራን ዳኞች ስልጠና እና ምክክር ተካሂዷል::

የስራ ክርክር ችሎቶች አስማሚ ረዳት ዳኞች የልምድ ልውውጥ መድረክ ተከናወነ።

811

የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳዮች በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ማዕቀፍ ውስጥ እንዲያልፉ በመመሪያ ከተደነገጉ የክርክር አይነቶች አንዱ ሲሆን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ካለው አጠቃላይ የስምምነት ውጤት ላይ የማይናቅ ድርሻ አለው፡፡

በኔትዎርክ እና ዳታ ሴንተር አስተዳደር ላይ ስልጠና ተሰጠ ፡፡

233

ለፌዴራል መጀመረያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድሬደዋ እና አዲስ አበባ ላሉ ሁሉም ምድብ ችሎት የኔትዎርክ ባለሞያዎች በኔትዎርክ እና ዳታ ሴንተር አስተዳደር ላይ ከታህሳስ 14 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ልደታ በሚገኘው በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ አፈፃፀም ፅህፈት ቤት 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የስልጠና ማዕከል ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

በወንጀል ፍትህ አስተዳደር የፍ/ቤቶች (የዳኝነት አካል ) ሚና በሚል ትምህርታዊ ገለፃ ተሰጠ ።

205

ትምህርታዊ ገለፃዉ የተሰጠዉ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ 3ኛ አመት የህግ ተማሪዎች ሲሆን ገለፃዉን የሰጡት የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ኘሬዝዳንት ክቡር አቶ ፋአድ ኪያር ናቸዉ።

ለክቡራን ዳኞች ውጤት እየተገለፀ ይገኛል::

790

የ2017 ዓ.ም የዳኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና ተካሄዶ ለክቡራን ዳኞች ውጤቱ እየተገለፀ ይገኛል::

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ባወጣው የዳኞች የስራ አፈጻጸም ምዘና መመሪያ ቁጥር 09/2015 መሰረት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ከጥቅምት 1/2017 እስከ ሐምሌ 30/2017 ባለው ጊዜ ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደው ምዘና ውጤት ለዳኞች የማሳወቅ ተግባር እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በመመሪያው መሰረት የዳኞችን የስራ አፈጻጸም 12 አካላቶች የሚመዝኑ ሲሆን እያንዳንዱ መዛኝ የሚሰጠውም ውጤት በመመሪያው ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚሁ አግባብ 157 ዳኞች የስራ አፈጻጸማቸው ተመዝኖ የተሰጠ ውጤት በአመራሩ በአካል ሊገለፅ እንደሚገባ በመመሪያው አንቀፅ 21 በሚገልፀዉ መሰረት የ2017 የምዘና ውጤት እንዲሁም የ3 ተከታታይ አመታት ዉጤት ማጠቃለያ በ7 ምድብ ችሎቶች ለሚገኙ ዳኞች ለእያንዳንዱ የማሳወቅ ተግባር ተከናውኗል::

123578910Last