በስነ-ምግባር፣ በመሪነት፣ በስነ-ስርዓት ህጎች ዓላማ አና መርሆች እንዲሁም በሬጅስትራር አሰራሮች ላይ
በሚስተዋሉ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ላይ ለሬጅስትራሮች ስልጠና ተሰጠ።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ለሚገኙ የሁሉም ምድብ ችሎቶች ሬጅስትራሮች ህዳር 26 እና 27 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መስሪያ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች እና ዳኞች አማካኝነት በሬጅስትራር አገልግሎት አሰጣጥ የሚጠበቅ ስነ-ምግባር ፣ ሬጅስትራሮች በዳኝነት ስርዓት ውስጥ ያላቸው የመሪነት ሚናን፣ በስነ-ስርዓት ህግጋት ዓላማ እና መርሆችን ከማሳካት አኳያ የሬጅስትራሮች ሚናን እንዲሁም በዳኝነት ክፍያ አፈፃፀም እና በሬጅስትራር አሰራሮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው በሚሉ እና በተለዮ ርእሶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የማነቃቂያ ስልጠና ተሰጠ።