የቅድመ-ክስ ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት አገር አቀፍ ኮንፈረንስ ተካሄደ።

1015

“የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች” ከ Agence Francaise de Development (AFD) በተገኘ ድጋፍ በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነ በቅድመ ክስ ሂደት በፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው ለሚገኙና ጠበቃ ለመቅጠር አቅም ለሌላቸው ተጠርጣሪዎች ነፃ የሕግ ድጋፍ አገለግሎት የመስጠት ፕሮጀክት ከ2014 ዓ.ም እስከ አሁን ተግባራዊ ሲደረግ የቆየ ሲሆን ይህንንም ስራ በአዲስ አበባ መስተዳደር ፣በሲዳማ ብሄራዊ ክልል እና በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል ውስጥ በተመረጡ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላትን በማቋቋም እና የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

መሪነት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና ስነ-ምግባር ላይ ስልጠና ተሰጠ።

1566

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለዋናው መስሪያ ቤት እና ለሁሉም ምድብ ችሎቶች ድሬደዋን ጨምሮ ለሚገኙ ቡድን መሪዎች፣ ሱፐርቫይዘሮች እና ሬጅስትራሮች ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መስሪያ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች አማካኝነት በመሪነት ሚና፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና ስነ-ምግባር ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በስልጠናዉ መርሃ-ግብር የተከበሩ አቶ ፉአድ ኪያር የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት በዳኝነት ስርአት ውስጥ የመሪነት ሚና በሚል ርእስ ለውጥን ከመምራት ጋር አያይዘው ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን በዚህም መሪዎች የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲያስችላቸው ባለ ራዕይ፣ ታማኝ፣ ተግባቢ፣ ርህሩህ፣ ትጉህ፣ ተላማጅ እና ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው በዚህም ለሌሎች መንገድ የሚያሳዩ እና አዎንታዊ ተፅእኖ የሚያሳድሩ መሆን እንዳለባቸው ከተቋሙ ስራ እና ከሰራተኞች አሰራር ጋር በማያያዝ አብራርተዋል።

የሴቶችና ህፃናት የወንጀል ችሎት ዳኞች ፎረም ውይይትና ስልጠና ተሰጠ

846

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሴቶችና ህፃናት የወንጀል ችሎት የዳኞች ፎረም የ2018 ሁለተኛው ውይይትና ስልጠና በቢሾፍቱ እየተካሄደ ይገኛል::

የስልጠናው እና የውይይቱን መክፈቻ ያደረጉት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ ሲሆኑ የዳኞች እርስ በርስ ውይይት እና ስልጠና መካሄዱ ተቀራራቢ የህግ አተረጓጎምና አሰራር እንዲኖር÷ ልምድና ክህሎት በማዳበር ቀልጣፋና ጥራት ያለው ዳኝነት ለመስጠት አስተዋፅዖ እንዳለው በመግለፅ በሀገር አቀፍና ሀገራችን ባፀደቀቻቸው ልዩ የሴቶችና ህፃናት ህጐች ውይይት እና ስልጠና መካሄዱ ዳኝነት ፈልገው የሚቀርቡ ሴቶችና ህፃናት መብታቸው እንዲረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅዖ እንዳለው ገልፀዋል::

4 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ ሲሸጥ የተያዘ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

1922

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት ግምቱ 38 ሚሊየን ብር የሆነ 4 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ ሲሸጥ የተያዘው ግለሰብ በእስራት እና በገንዘብ እንዲቀጣ ወሰነ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ሆሞሻ ወረዳ ነዋሪ የሆነው መሀመድ ሳሊህ መሀመድ ላይ ክስ የመሰረተው በፍትህ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ነው።

ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ ግለሰቡ ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 6 ሰዓት ሲሆን በአሶሳ ከተማ ልዩ ስሙ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ በተደረገ ክትትል በተሰጠው የወርቅ አቅራቢነት ፍቃድ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ለሰጣቸው አካላት ብቻ ወርቁን መሸጥ ሲገባዉ በባንክ ፍቃድ ላልተሰጠው አካል ወርቅ ለማስተላለፍ ሲሞክር እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡

አዲስ በወጡ መመሪያዎች ላይ ገለፃ እና የእቅድ ውል ስምምነት ተካሄደ

1695

የፀደቁ መመሪያዎችን በአግባቡ መተግበር እንደሚገባም ተገለፀ።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ በፀደቁ መመሪያዎች በአግባቡ እንዴት መተግበር እንዳለባቸው እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም የውል ስምምነት ሰነድን አስመልክቶ ከየምድብ ችሎቶቹ ተጠሪ ዳኞች፣ ዋና ሬጅስትራር፣ ዳይሬክተሮች፣ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና የቡድን መሪዎች ጋር ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ልደታ በሚገኘው የዋናው መስሪያ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተደረገ።

በእለቱ በነበረ መርሃ-ግብር የተከበሩ ፉአድ ኪያር የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት በእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸው ወቅት መመሪያ ላይ ተንተርሶ አሰራርን ወጥ ለማድረግ ፤ በውል ስምምነት መሠረት ስራን ቆጥሮ ለመቀበል እና ለመመለስ፤ እንዲሁም ሌሎች መነሳት በሚገባቸው ነገሮች ላይ ለመወያየት መድረኩ መመቻቸቱን ተናግረው መርሃግብሩን አስጀምረዋል።

የሴቶችና ህፃናት የወንጀል ችሎት የዳኞች ፎረም የ2018 የመጀመሪያው ውይይትና ስልጠና በቢሾፍቱ እየተካሄደ ይገኛል

485

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሴቶችና ህፃናት የወንጀል ችሎት የዳኞች ፎረም የ2018 የመጀመሪያው ውይይትና ስልጠና በቢሾፍቱ እየተካሄደ ይገኛል::

የስልጠናው እና የውይይቱን መክፈቻ ያደረጉት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ ሲሆኑ የዳኞች እርስ በርስ ውይይት እና በመረጧቸው ርዕሰ ጉዳዮች ስልጠና መካሄዱ ተቀራራቢ የህግ አተረጓጎምና አሰራር እንዲኖር÷ ልምድና ክህሎት በማዳበር ቀልጣፋና ጥራት ያለው ዳኝነት ለመስጠት አስተዋፅዖ እንዳለው በመግለፅ በሀገር አቀፍና ሀገራችን ባፀደቀቻቸው ልዩ የሴቶችና ህፃናት ህጐች ውይይት እና ስልጠና መካሄዱ ዳኝነት ፈልገው የሚቀርቡ ሴቶችና ህፃናት መብታቸው እንዲረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅዖ እንዳለው ገልፀዋል::

ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ሁነቶች ምዝገባና የነዋሪዎች መረጃ ኤጀንሲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተደረገ

480

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ሁነቶች ምዝገባና የነዋሪዎች መረጃ ኤጀንሲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት በድሬዳዋ ከተማ ተፈረመ፡፡ ስምምነቱ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎት የሚሰጡ የፍቺ እና የጉዲፈቻ ውሳኔዎች በፍርድ ቤቱ በሚዘጋጁ ማዕከላት የምዝገባ አገልግሎቶችን ባለጉዳዮች እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን በዚህም የተገልጋዮችን ጊዜ እና ገንዘብ በመቆጠብ መጉላላትን የሚያስቀር ይሆናል፡፡

የድሬዳዋ ምድብ ችሎት የ2018 የሩብ ዓመት አፈፃፀም እና የዕውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር ተካሄደ--

788

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች÷ ክቡራን ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ረዳት ዳኞች÷ ሰራተኞች በተገኙበት በድሬዳዋ ከተማ የፍርድ ቤቱ የ2018 ዕቅድ እና የሩብ ዓመት አፈፃፀም በፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ ቀርቧል:: እንዲሁም የድሬዳዋ ምድብ ችሎት የሩብ ዓመት አፈፃፀም በምድብ ችሎቱ ተጠሪ ዳኛ ደመቀ መኮንን ቀርቧል::

የ2018 ዕቅድ ÷ የሩብ ዓመት አፈፃፀም÷ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዳኞች÷ ምድብ ችሎቶች÷ ባለሙያዎች÷በጡረታ ለተለዩ ዕውቅናና ምስጋና ስነ ስርዓት ተካሄደ---------------------------------------------------------

529

የ2018 ዕቅድ ÷ የሩብ ዓመት አፈፃፀም÷ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዳኞች÷ ምድብ ችሎቶች÷ ባለሙያዎች÷በጡረታ ለተለዩ ዕውቅናና ምስጋና ስነ ስርዓት ተካሄደ---------------------------------------------------------

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሩ÷የቋሚ ኮሚቴው አባላት ፣የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ፣የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባላት፥ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን÷ የፌደራል የማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል የኑስ ÷ የፌደራል የጠበቆች ማህበር ፕሬዚደንት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው÷ ክቡራን ተጠሪ ዳኞች፣ ክቡራን ዳኞች፣ ሬጅስትራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ረዳት ዳኞች በተገኙበት በሸራተን አዲስ ሆቴል የፍርድ ቤቱ የ2018 ዕቅድ እና የሩብ ዓመት አፈፃፀም ቀርቧል::

መክፈቻ በማድረግ የጀመሩት የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር ፍርድ ቤቱ በ2017 ዓ.ም ውጤታማ የዳኝነት አገልግሎት የሰጠ መሆኑን በየደረጃው ሲካሄዱ የነበሩ የተገልጋይ እርካታ ጥናት÷ የዳኞች ምዘና ውጤት እና ግምገማዎች የሚያመለክቱ መሆኑን ገልጸው ለዚህም የፍርድ ቤቱ ክቡራን ዳኞች፣ ተጠሪ ዳኞች፣ የጉባኤ ተሻሚዎች እና የፍርድ ቤቱ ሰራተኞች ለነበራቸው አስተዋጽኦ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ በጀት ዓመት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር መመሪያን በጥበቅ መተግበር፣ የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ይበልጥ ማከናወን፣ የተገልጋይ እርካታ ጥናት በውስንነት በተነሱ በዳኝነት ጥራት÷ ስነምግባር ÷ ተገማችነት ላይ እየተነሱ የሚገኙ ቅሬታዎች መቀነስ ላይ ትኩረት ማድረግ የሚገባ መሆኑን አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

የፍርድ ቤቱ የ 2018 በጀት ዓመት እቅድ እንዲሁም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም በፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ ቀርቧል::

የሰንደቀ ዓላማ ቀን እና የችሎት መክፈቻ መርሃ-ግብር ተከናወነ፡፡

1120

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰንደቅ ዓላማ ቀን እና የችሎት መክፈቻ መርሃ ግብር በደማቅ ስነ-ስርዓት ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መስሪያ ቤት እና ልደታ ምድብ ችሎት ተከናወነ፡፡በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰንደቅ ዓላማ ቀን እና የችሎት መክፈቻ መርሃ ግብር በደማቅ ስነ-ስርዓት ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም በዋናው መስሪያ ቤት እና ልደታ ምድብ ችሎት ተከናወነ፡፡

First2345791011Last