የፌ/መ/ደ/ፍርድ ቤት ዓመታዊ የአስተዳደር ሰራተኞች በዓል እና የችሎት መክፈቻ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ

506

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአስተዳደር ሰራተኞች ዓመታዊ በዓል እና የችሎት መክፈቻ ከአንድ ሺህ በላይ ሰራተኞች፥ ክቡራን ፕሬዝዳንቶች፥ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሠው ሀብት ስራ አመራር ጉባዔ አባላት ክብርት ወ/ሮ ከዲጃ ያሲን እና ክቡር ዶ/ር ከበደ ገነቴ÷ አስተባባሪ ሬጅስትራሮች ፣ ዳይሬክተሮች ÷ ሬጅስትራሮች እና የስራ ክፍል ኃላፊዋች በተገኙበት በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋና መስሪያ ቤት ግቢ ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም እየተከበረ ይገኛል።

የአቃቂ ቃሊቲ እና የንፋስ ስልክ ምድብ ችሎቶች የስራ ጉብኝት ተካሄደ::

985

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ÷የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ እንዲሁም ሌሎች የፍርድ ቤቱ አመራሮች በተገኙበት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ እንዲሁም ንፋስ ስልክ ምድብ ችሎቶች አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም በተለይም ከቴክኖሎጂ ትግበራ ዝግጁነት አንፃር ጉብኝት የተከናወነ ሲሆን በሁለቱ ምድብ ችሎቶች ሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግና ወደ ሌሎች ለማስፋፋት በሚያስችል የግብአት÷ የሰው ሀይል÷ የግንዛቤ ማስጨበጥ እንዲሁም የልምድ ልውውጥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ በአጭር ቀናት በሁለቱ ምድብ ችሎቶች ሙሉ ትግበራ ስለሚደረግበት ሁኔታ ውይይት ተደርጓል::

በሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ።

848

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በሴቶች እና ህፃናት ባጠቃላይ ልዩ ድጋፍ በሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የተቀላጠፈ፣ ጥራት ያለው ፣ ተደራሽ፣ ውጤታማ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ፣ በዳኝነት ሂደት እና በኃላ ለህፃናት እና ሴቶች የተቋማቱ ተቋማዊ ነፃነት በጠበቀ በህግ ማሻሻያዎች፣ በስልጠና፣ በሙያ ፣ግብዓት ፣ ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ሌሎች ብርክት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ውይይት ተደረጎ ቀጣይ ቅንጅታዊ ስራዎች በተመለከተ የመግባቢያ ስምምነት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ፎዓድ ኪያር ተፈርሟል፡፡

በኘሮግራሙ ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ የፌ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ከሴቶችና ህፃናት አኳያ ያከናወናቸው፣ ቀጣይ ለመስራት የታቀዱ እንዲሁም የመግባቢያ ስምምነት ይዘት በዝርዝር አቅርበዋል::

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሴቶችና ህፃናት ለተለያዩ ጥቃቶች የሚጋለጡበትና ውስብስብ ለሆኑ ችግሮች የሚዳረጉበት ሁኔታ መኖሩን ገልፀዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍትህ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሰፉፊ ስራ እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

የአመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ::

704

በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለተከታታይ 3 ቀናት ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ:: "የፍትህ አካላት ሚና በሀገረ መንግስት ግንባታ" በሚል ርዕስ የተጀመረው ስልጠና በመቀጠል በፍትህ አካላት አመራር ክህሎት ÷ Leadership Style÷ Growth mindset and emotional Intelligence በሚሉ ርዕሶች ስልጠናው ተሰጥቷል::

አጠቃላይ የጤና ምርመራ በነፃ ለዳኞች

986

የፌደራል የመ/ደ/ፍ/ቤት ከኢ.ፌ.ድሪ የጤናሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለፌደራል ፍ/ቤት ዳኞች እና ቤተሰቦቻቸዉ ነፃ አጠቃላይ የጤና ምርመራበመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ፍ/ቤቱ ከኢ.ፌ.ድ.ሪ የጤና ሚኒስቴር የኮተቤ ኤካ ሆስፒታል ጋር በመነጋገር በዳኞች የመኖሪያ ግቢ አፖርታማ ግዚያዊ የምርመራ ክሊኒክ እና ላብራቶሪ በማቋቋም ከነሀኔ 19-21/2017 የሚቆይ ነፃ ሕክምና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በሦስት ቀናት የሚሰጡትሕክምና አገልግሎቶች የጠቅላላ ምርመራ፣የአይንህክምና፣የልብ ምርመራ እና አልትራ ሳውንድ፣የማህፀን ፅንስ ምርመራ፣የሕፃናት ሕክምና፣የቆዳሕክምና፣ላብራቶሪ፣ ቀላል ቀዶ ጥገና እና የጤና መረጃ እና ሌሎች ተያያዥ ሕክምናዎች ናቸዉ፡፡

የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ዋና መ/ቤት ሊያስገነባ ያሰበው ሕንፃ የመጀመሪያ ዲዛይን ለውይይት ቀረበ::

940

የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ዋና መ/ቤት ሕንፃ ለማስገንባት ከኢትዬጰያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር በግንቦት ወር የሕንፃውን ዲዛይን አፈር ምርመራ እና ውል አስተተዳደር ስራዎችን ለማከናወን ውል መገባቱ ይታወሳል፡፡

የስፖርት ማዘውተሪያ (ጂም)÷ ስቲም÷ሳውና ባዝ÷ የውስጥና የውጪ ህንፃ እድሳት÷ መሰብሰቢያ አዳራሽ ስራ ተጠናቆ ተመረቀ::

534

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋና መስሪያ ቤት እና የልደታ ምድብ ችሎት የስፖርት ማዘውተሪያ (ጂም)÷ ስቲም÷ሳውና ባዝ ÷የውጪና የውስጥ ህንፃ እድሳት÷ መሰብሰቢያ አዳራሽ ስራ ተጠናቆ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ÷ የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ፣የፌደራል የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባላት÷ የፌደራል ጠበቆች ማህበር ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው÷ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት÷ የበላይ ሀላፊዎች÷ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንት ፅ/ቤት ሀላፊዎች÷ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሀላፊዎች÷ ተጠሪ ዳኞች÷ ክቡራን ዳኞች÷ ዋናና አስተባባሪ ሬጅስትራሮች÷ ዳይሬክተሮች ÷ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምረቃ መርሀ ግብር ተካሂዷል::

ጥናቱ ደረጃዉን በጠበቀ ህትመት ታትም ለስርጭት በቃ *

1518
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚሰጠው የዳኝነት አገልግሎት በሚመለከት ያካሄደውን የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት ደረጃዉን በጠበቀ ህትመት አሳትሞ ለስርጭት አብቅቷል ።
ፍ/ቤቱ በ2017 ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ያስጠናዉን የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት በአዲስ አበባ እና በድሬደዎ ከተማ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር መወያየቱ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱም በቀረበው የጥናት ሰነድ ላይ ባለድርሻ አካላት አስተያየት የሰጡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ያለበትን ደረጃ ጠንካራ እና ደካማ ጎን በዚህ አግባብ መለየቱ እጅግ የሚያበረታታ ተግባር መሆኑን፣ ጥናቱ ፍርድ ቤቱ ያለበትን ደረጃ ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ የሚመለክት በመሆነ ቁቡልነት እንዳለው በማንሳት በቀጣይ የጥናቱን ግኝቶች በመውሰድ አቅዶ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ መግለፃቸዉ ይታወሳል።

ዓመታዊ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቀቀ ::

957

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር፣ ምክትል ፕሬዚዳንት አሸነፈች አበበ÷ የሁሉም ምድብ ችሎቶች ተጠሪ ዳኞች÷ ዳይሬክተሮች÷ አስተባባሪ ሬጅስትራሮች እና ቡድን መሪዎች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ የተካሄደ ሲሆን ግምገማው በቅድሚያ በየምድብ ችሎቱ፣ በየዳይሬክቶሬቱ እና በየስራ ክፍሉ ከበጀት ዓመቱ ዕቅድ እና በተላኩ ግምገማ መስፈርቶች መሰረት ያደረጉትን የግምገማ ሪፖርት የእያንዳንዱ ምድብ ችሎት ሀላፊዎች እና የ ስራ ክፍል ሀላፊዎች ዓመታዊ የስራ አፈፃፀማቸውን ሪፖርት በማቅረብ የተጀመረ ሲሆን በመቀጠል በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ የጋራ ውይይት÷ አስተያየቶች እና ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

First34568101112