2ኛው ልዮ የህፃናት እና የሴቶች ችሎት በየካ ተመረቀ

1085

በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት 2ኛው ልዮ የህፃናት እና የሴቶች ችሎት የተመረቀ ሲሆን በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ፎዓድ ኪያር÷ ምክትል ፕሬዚደንት አሸነፈች አበበ÷ የአዲስ አበባ ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ሀላፊ ቆንጂት ደበላ÷ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዳኛ ተክለሃይማኖት ዳኜ ፣ ክቡራን ዳኞች÷ የUNICEF Ethiopia ሀላፊዎችና ባለሙያዎች÷ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ የፍትህ ሚኒስቴር ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሀላፊዎች÷የፍርድ ቤቱ ሬጅስትራሮች÷ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል::

ሬጅስትራሮች በአዲሱ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝት ክፍያ ለመወሰን የወጣውን የዳኝነት ክፍያ ደንብ ቁጥር 1/2017 ማብራሪያ እና በደንብ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡

826

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት የዜጎችን ፍትህ በማይጋፋ መልኩ ተመጣጣኝ የዳኝነት ክፍያ ለማስከፈል፤የዳኝነት ክፍያን በማሻሻል የዳኝነት አገልግሎቱን  ዘመናዊ እና ቀልጣፋ እንዲሆን ለማስቻል እንዲሁም የፍትህ ስርአቱ ለዜጎች ተደራሽ እንዲሆን የክስ ምክንያት የሌላቸውን ጉዳዮች ወደ ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ በማድረግ የዳኝነት የስራ አካባቢ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ለማድረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲስ ደንብ  መዉጣቱ ይታወቃል፡፡  በዚህዉ መሰረት የፌዴራል  ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያ ደንብ ቁጥር 1/2017 በተመለከተ ከዚህ ቀደም በየምድብ ችሎቱ ለሚገኙ አስተባባሪ ሬጅስትራሮች እና የፋይናንስ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨመጫ ስልጠና የተሰጠ መሆኑ ይታወቃል

ፍርድቤቱ የማህበራዊ ሳይንስ ዳይሬክቶሬት አዲስ ለተቀጠሩ ባለሙዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

1000

የማህበራዊ ሳይንስ ዳይሬክቶሬት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማለትም በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ ዳሰሳ ጥናት፤ በወንጀል ነክ ጉዳዮች ገብተው የተገኙ ከ9 እስከ 15 እድሜ ያሉት ህጻናትን በተመለከተ የባለሙያዉ ሚና፤ የህጻናት ጥቃት ምንነት፤ የማህበራዊ ሳይንስ  ባለሙያዎች ሚናቸዉ፣ የስነ ምግባርና የተግባቦት ክህሎትን ማደበር በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ከሰኔ 11/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታይ 5 ቀናት አዲስ ለተቀጠሩ የማህበራዊ ሳይንስ  ባለሙዎች   በፍርድ ቤቱ ዋና መ/ቤት  ስልጠና ሰጥቷል፡፡ 

የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት

3104

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚሰጠው የዳኝነት አገልግሎት በሚመለከት ያካሄደውን የተገልጋይ ዳሰሳ ጥናት የኢፌድሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ፣ የምክር ቤቱ የህግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ኢሳ ቦሩ፣ ክቡር አቶ ተኸሊት ይመስል፣ የኢፌድሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ፣ የሕግና ፍትሕ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ፣ የተለያዩ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ተቋማት ኃላፊዎች፣ የተለያዩ ማህበራት ተወካዮች፣ የፍርድ ቤቱ ተጠሪ ዳኞች፣ አስተባባሪ ሬጅስትራሮች፣ ዳይሬክቶሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አቅርቧል፡፡

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታ

1543

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋና መስሪያ ቤት እና የልደታ ምድብ ችሎት በአንድ ሕንጻ ላይ በመሆኑ ምክንያት ከፍተኛ መጨናነቅ፣ በቂ የችሎት አዳራሽ እንዳይኖር እና ለተገልጋይ ምቹ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡

ይህን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት ፍርድ ቤቱ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ሰፊ ውይይቶች እና ምክክሮች ካደረገ በኃላ በተፈቀደው መሰረት የፍርድ ቤቱ ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ለመገንባት በሂደት ላይ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር እና የህንጻ ግንባታውን በሚመለከት የዲዛይን፣ አፈር ምርመራ እና የውል አስተዳደር ስራዎችን ከሚያከናውነው የኢትዮዽያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ኃላፊ ኢንጀነር አንዋር ካሳሁን ጋር ውል ተፈራርመዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሀላፊዎች የችሎት ጉብኝት እና ቅንጅታዊ ስራ ውይይት ተካሄደ

938

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እና ሌሎች ሀላፊዎች ፣ የፌደራል

የ2017 የ9ወር የዕቅድ አፈፃፀም ውይይት መድረክ ተካሄደ

1114

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ፉዓድ ኪያር፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች÷ የሁሉም ምድብ ችሎቶች ተጠሪ ዳኞች፣ ዳይሬክተሮች እና ሬጅስትራሮች በተገኙበት የፍርድ ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የ9ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።

የቅንጅታዊ ስራ የአፈጻጸም ግምገማ

827

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ባደረገው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት ባለፉት ሶስት ወራት በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ የፍቺ እና ጉዲፈቻ ወሳኝ ኩነቶች ምዘገባን በሚመለከት የተሰራው ስራ የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ ኮርት ማናጀር፣ ተጠሪ ዳኞች እና አስተባባሪ ሬጅስትራሮች እንዲሁም በኤጀንሲው በኩል የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ የክፍለ ከተማ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት የአፋጻጸም ግምገማ አካሄዷል፡፡

First3456791112